
መ ጠ ሪ ያ
..ስማ አንተ ..ብሎ የሚጠራ ሰው እንዴት ያበሽቀኛል መሰላችሁ ፡፡ እንዲህ ዓይነቱን ሰው ማንኛችንም ብንሆን የምን ገምተው ስነስርዓት የሌለው በጭንቅላቱ ከሚያስብ ይልቅ በጡንቻው የሚያስብ አርገን ነው፡፡ ሁለችን ማንሆን እንካን አብዛኞቻችን ፡፡
አዋ የስም ነገር ይከነክናል ፡፡ በየትኛውም አገር በሚገኝ መዝገበ ቃላት ውስጥ ከስማችን የሚበልጥ ቃል እናገኛለን? አይመስለኝም ፡፡ ስማችን አብሮን ይወለዳል አብሮን ይኖረል ፡፡ በመጨራሻም አብሮን ይሞታል ፡፡ የአንዳንዶቻችን ማለቴ ነው ፡፡ የአንዳንዶች ስም ደግሞ ባለቤቱ ከኖረበት የሕይወት ዘመን በላይ ይኖራል ፡፡ ይሄም የስሙ ባለቤት ለስሙ መዘከሪያ የሚሆን ስራ ሰርቶ አልፋል ማለት ነው፡፡
ስሞች እንደ ጊዜው የመልክዓ ምድር አቀማመጥ ፋሸን መደብ/ የኑሮ አቃም / ሙያና ትምህርት የተለያዩ ናቸው፡፡
በውሉ አስተዳደር ክልል የስሞች አደራደር ትንሽ ለየት ያለ ነው፡፡ አባትና ልጅ የክርስቲያን ስም ኖራቸው አያት ላይ ሲሰልሙ አንስማለን ፡፡ መላኩ ጌታቸው ሁሴን መሐመድ ይመር ..ወዘተርፈ ፡፡
በደቡብ ሸዋ ስንመለከት በከምባታና ሐድያ ዮሐንስ ሐንቆሬ ዳዊት ላጲሶ የመሳሰሉትን ስሞች እንሰማለን ፡፡ይሄ ሁኔታ በአካባቢው ካሉደት የወንጌላውያን ትምህርት ሥርጸት የስሞች ሁኔታ እየተዳቀለ መምጣቱን መገንዘብ ይቻላል ፡፡
ቆየት ባለው ጊዜ አንድ ህጻን ሲወለድ የአያቱን ስም ካልሆነም የቅርብ ዘመዶቹን ወይም ደግሞ በተወለደበት ቀን ጋር በሚገጥመው በመልአክ ስም ስያሜ የጠራ ነበር ፡፡ ስም አውጪዋቹም ክርስትና አባት ቄሶች እና ለቤተሰቤ ጥሩ የሚመኙ ሁሉ መሆን ይችላሉ፡፡
የስሞች አሰያየም ከጊዜው ጋር እየተቀያየረም ይመጣል ፡፡ በአንድ ወቅት ዳዊት የሚለው ስም በዛ ያለ ሆኖ ቢታይም በሌላ ጊዜ ደግሞ ሰለሞን የሚለው በልጦት ይታያል ፡፡ በየጊዜው ዝና የሚያገኙ ሰዋች በአንዳንድ አካባቢዋች ላይ ተጽጽኖ ይኖራቸዋል ፡፡ ከዚህ ሌላ በሀገራችንም ቢሆንክ ጊዜው ጋር እየመጡ ያሉ ስሞች ይስተዋላሉ ፡፡ እንደ አብዮት ታገል የመሳሳሉት ፡፡
የዘመኑ ልጆች ሌላም ዓይነት የስም አሰያየም በፍቅር ይዘውታል ፡፡ ቲቲ ቢቢ ቺቺ ኩኩ ቡቡ ኬቲ ቤቲ ናቲ …. ወዘተ አንዳንድ ስሞች በእውነቱ ከሆነ የውሻ ይሁን የድመት ወይም የመኪና መለያ የላቸውም ፡፡ ለነገሩማ ከበቡሽ ታደለ የምትባለዋም ወጣት የስማን የመጀመሪያ እንግሊዝኛ ፊደል ከአባታ ስም የመጀመሪያ እንግሊዝኛ ፊደል ጋር በማገናኘት ኬቲ ተሰኛለች፡፡ የዘልማድ ሆኖብን በፈረንጅ ስም የሚጠራ ሁሉ መልኩም ቆንጆ እየመሰለን፡፡ /ፈረንጅ ሁሉ ቆንጆ ነው ያለን ማን እንደሆነ ባላውቅም ኬቲ ወይም ሱዚ /በጋደኞቻ / ተሰኚዋን ግንባር ለግንባር ስናገኛት በሳ ቦታ የምናፍር አለን ፡፡
ልጆች ሆነን ካስ ስንጫወት አንድ ጋደኛችንን ሳሚ እያልን ነበር ፡/ሳሙኤልን / በማሳጠር የምንጠራው፡፡ ይሔን የሰማ አንድ ተንኮለኛ ካሱን ትቶ ወገቡን በመያዝ …አሁን አንተን ነው ሳሚ ቢገዛማ ቡቡ ነበር የምትባው ..ያለው ትዝ ይለኛል ፡፡ አሁን ቡቡ የሚለው ስምም ቆንጆና ተፈላጊ ስም /በዘመኑ ልጆች/ ሊሆን ፡፡
ወላጆች አልፎ አልፎ ልጆቻቸው ከሌሎች ልጆች ለየት ያሉ እንዲሆኑላቸው ስለሚፈልጉ የተለየ ስም ያወጡላቸዋል፡፡ የኃላ የኃላ ልጆቻቸውን ሊጎዳም እንደሚችል ባለመገንዘብ፡፡ እነዚህ የተለየ ስም ያላቸው ልጆች በማህበራዊ ኑሮአቸው ወስጥ ከእድሜ ገደኞቻቸው ለየት ባ ሁኔታ ያድጋሉ ፡፡ ተነጫናጭና ለየት ያሉ፡፡
እንዲህም ሲባል ለየት ያለ ስም ያላቸው ሙሉ በሙሉ ጸባያቸው በዚህ መልክ ይቀረጻል ማለትም አይደለም፡፡ ብዙዋቹ ግን ስማቸው የሚሰጣቸው ስሜት አናናራቸውንም በዛው ያድጋል ፡፡ በሴት ስም የሚጠሩ ወንዶችን ብንወስድ በልጅነታቸው መሰቂያ ስለሚሆኑ ለየት ያሉና ዝምተኞች ይሆናሉ ፡፡ ብዙ ጊዜም ከማህበረሰቡ የሚገለሉበት አጋጣሚም አለ፡፡ ደም መላሽ ገነነ…የመሳሰሉት መጠሪያ ያላቸው ልጆች በአብዛኛው ጠበኞች ናቸው፡፡ ሌላው ቢቀር እኔን ያገጠሙኝ ፡፡
በቺካጎ የሎዮላ ዮኒቨርስቲ የስነ ልቡና ጠበብቶች ዶ/ር ሮበርት ኒኪላይ አርተር ሃርትማን እና ጄሴ ቨርሊ የስነ ልቡና ህመም ፍርድ ገዳዮችን ሲመረምሩ ሰማንያ ስምንት የተለየ ስም ያላቸውንና እንዲሁም ሰማንያ ስምንት የአዘቦቱ ቀን ስም ያላቸውን በማጥናት ፡፡….
……የተለዪ ስሞች ከጤነኞች መህበራዊ ግነኙነቶች ጋር ይጋጫሉ ፡፡ ይህም የተረበሸ አቃም ይፈጥራል አንድ ህጻን ልጅ የሚያርፍበት ዓይነት ስም የሚያደናግር የወንድ ወይም የሴት መሆኑ የማይታወቅ ዓይነት ስም ቢሰጠውና መሳቂያ ቢሆን ለስሙ ሁልጊዜ እንደተጣላ መኖር ስላለበት ስሜታዊ እግሮች ሊከሰቱበት ይችላሉ፡፡ .. የሚል መደምደሚያ ላይ ደርሰዋል ፡፡
ስሞችን ለህጻናት በምንሰጥበት ወቅት ካደጉ በኃላ በማህበራዊ ኑሮ ውስጥ በምይዙት ቦታ የስነልቦና ችግር እንዳይገጥማቸው የግዜውን ሁኔታ(ፋሽኑ )በመከተል በጣም የተለየም ስም ሳይሆን በጣም ብዙ ህጻናት የሚጠሩበትም ያልሆነ ለጆሮ ደስ የሚል ሲያሜ ልናደርገው ለነገው ማሙሽ ቨስነልቦናዊ አቃም ይረዳዋልና እናስብበት ፡፡
የስም ነገር ከተነሳ በቅርቡ የሰማሁት ደግሞ ጊምቢ /በወለጋ አስተዳደር ክልል / የምትገኝ አውራጃ/ አካባቢ ሚስት ባላን በጣም ትልቅ ችግር ላይ ካልሆነች በሰተቀር በስሙ እንደማትጠራው ነው ፡፡ ሌላው ቀርቶ ጎረቤት አካባቢ የባላ ሞክሼ ትንሸ ልጅ እንካን ቢኖር እራሳ ስም አውጥታ ትጠራዋለች እንጅ በውነተኛ ስሙ አትጠራውም ይባላል፡፡ ሆስፒታል ልጃን ለማሳከም ሄዳ የልጃን ስም አስመዝግባ የአባቱን ስም ስትተየቅ እንካን በአካባቢም ዘመድ ወደ ጎረቤቶች ከሌሉ እሳ ጨጥ ነው ፡፡ ብቻ አሁን አሁን የሴቶችንም ማህበር ስለተመሰረተ በስብሰባቸው ላይ ማህበራዊ ጉዳዮችን እያነሱ መወያየት ስለጀመሩ ይህ ልምድ እየተተወ ነው፡፡
እናቶቻችንስ በየቤቱ የማታጠፋዋን እህል ፈጅ ያቺ ሴትዮ የእከሌ ሚስት እመቤቲቱ እያሉ የሚጠሩት ለምንድን ነው ? ተስታችሁ እንካን ……… አይጣ ካላችሁ ስምህን ቄስ ይጥራው እሳ በሰም አትጠራም ተብላችሁ አልተገሰጻችሁም? የጊምቢ አካባቢ ሴቶች ባሎቻቸውን በስም አለመጥራታቸው ከእህል ፈጃ ጉዳይ ጋር የተያያዘ ነገር ይኖራል ?
እኔ እስካሁን የደረስኩበት ነገር የለም እናንተ ካወቃችሁ ግን አደራ ሹክ በሉን ጣጥፋችሁ፡፡