Powered by Bravenet Bravenet Blog

Tag Board

This tag board is currently empty.

Please type in the four characters shown in the black box.

Wednesday, February 18th 2009

8:07 AM

The critic

ሃያስውና ትችቱ

ሃያሲያን ብዙ አይነት ቢሆኑም በአንድ ነገር ይመሳሰላሉ ፡፡ ተቃውሞአቸውን በመግለጻቸው አልፎ አልፎ ሃሞታቸው መረር ያለው ሃያሲያን አልታጡም ፡፡ ጃክ ሻቼ የተባለው ስረ ፓሪስ ቲያትር ቤት መድረካ ላይ ሸጉጥ ይዞ በመውጣት እሱ በጠላው ድራማ የሚያጨበጭቡትን ተመልካቾች ያስፈራራ ነበር በዘመናችን ያሉ የስነጽሁፍ ሃያሲያን በቃላት ብቻ መወሰናቸው ተመስገን ነው፡፡

 

 አንዳንድ ሃያሲያን የጽሁፍን ባለቤት በግል የሚያውቁትን የማይወዱት ከሆነ የጭቃ ጅራፋቸውን ያነሱበታል መተቸት ያለበት ግን የተጻፈው ጽሁፍ ብቻ ነበር ፡፡ በሀገራችን ቆየት ባለው ጊዜ በእንደዚህ አይነተ ሃያሲያን መብዛት ሳይሆን ይቀራል መንግስቱ ገዳሙ.. አሳማና ድመት.. በምትለው መጻህፋቸው ውስጥ ባስቀመጡት ማስታወሻ .. አንድም የሚያስቀው አንዱን ያስተከዘው ይሆናል ፡፡ አንዱን የሚያስደነግጠው አንዱን ወደግል ስሜቱ ያመራውና የገዛሀሳቡን በመዘርጋት ልዩ ትርጉም ይሰጠው ይሆናል ይሁን እነጂ ደራሲው በትርፍ ሰአቱ በፊደል አጣጣል አንደመጣለት የጻፈው ነውና ምናልባት ተሳስተሀል የሚለኝ ቢገኝ እኔ እሱ እሱ እኔን ያለመሆኑ ለማስረዳት አልሰንፍም ፡፡ ብለው የጻፉት ወደው አይደለም ፡፡

 

ሌሎች ደግሞ ከጸሐፊው ጋር ባላቸው ትውውቅ የተነሳ እንዲያው በደፈባው4 የሙገሳ ጽሑፍ ያቀርባሉ፡፡ ወጣም ወረደ ግን ጽሁፍ ያዘለውን ፍሬ ነገርም ሆነ ፍሬ ፈርስኪ ቅንጣት ያህል አይለወጥም፡፡ መልእክቱ በተደራሲው የማገናዘብ ችሎታ እየተጣራ ይሰለቀታል ፡፡

 

ለመጻፍ ያነሳሳኝ ዋባው ነጥብ የአንድ ጋደኞዮ የየጊዜው ትችቱ እያስገረመኝና እያሳቀኝ ሲኖር በሮበር ኤንድ አዘር ኪዮሩሪ የዚቲስ በምለው መጽሀፍ ውስጥ ስለ ሃያሲያን የተጠናከረውን ካነበብኩ በኃላ ነው፡፡ ያነበብኩትን የጹሑፍ መጨረሻው ላይ አጋራችኃለሁ ፡፡ አሁን ግን ስለ ሃያሲው ጋደኛዮ በጥቂቱ ፡፡

 

ስለጋደኛዮ መልኩና ቁመናው ባልነግራችሁ ይሻላል ፍቅ ር እንዳያሲዛችሁ ፡፡ አቀራረቡም እንደው ዝም ነው፡፡ ብቻ ምን አለፋችሁ ገና ሰላም ስለው ትችቱ ከሰላምታዮ ይጀምራል በሳቅ እየተጀበ /በመጥፎ አይደለም ከመቀራረብ የተነሳ ነው/ ትንሽ ወረቀት ብጤ በጄ ከያዝኩ . መቼም የሚነበብ ነው. በማለት በፈገግታው ይቀበለኛል ፡፡ ፈገግታው እንግሊዞች disarming የሚሉት ዓይነት ነው፡፡ ትቅ አስፈቺ የሚለው አማርኛችን ይፍታው ይሆን?የተገናኘ ነው በምሣ ሰዓት ከሆነ እራት ሰዓት ላይ ብመልስልህስ ?ይላል ከዛ ፈገግታው ጋር . እሽግን አስተያየትህንም በጽሁፍ ብጤ ጨምረህ ብትሰጠኝ . እለዋለሁ ፡፡ እኔም አንደሌላው ጊዜ ከአስተያየቱ ጋር ሲመልስልኝ ታዲያ ማታውን በሙሉ መሳቅ ነው፡፡ ኮስተር ያለ ጸሐፊ ነኝ የምል ብሆን ኖሮ ገና በመጀመሪያው አስተያየት ገመድ ልፈልግ ሳልሄድ ቀረሁ ብላችሁ ነው ፡፡

 

አንድ ጊዜ የመድረክ ዝግጅት ነበረብኝና ያጠፋሁት ካለ ብታርመኝ ብዮ ጋብዝኩት ፡፡ ዝግጅቱ ሲያልቅ ምን አለኝ መሰላችሁ ..ደህና ትፈጨረጨሪያለሽ ..

 

ደህና ነው ያልኩትን አጭር መጣጥፍ ካነበበ በኃላ በጻፈልኝ ማስታወሻ ….. ብለህ የሰየምከው ጹሁፍህ በዚያ ሰሞን ጠፍቶብኝ እነደ ነበርና በኃላ እንዳገኘሁት ያወጋሁህ ይመስለኛል ፡፡ አስተያየቴን በአንድ አጭር ጨረፍተ ነገር ላጠቃለው ፡፡

 

..አንደጠፋ ቢቀር ይሻል ነበር ፡፡.. የሚል የነበባል ፡፡ ያልጠበቅኩት ዓይነት ትችት ስለሚሆን ብቻ የሳቅ ሴሌቼን ይኪረከኩራቸዋል ፡፡ በቀልድ መከሸንም ያውቅበታል ትችቱን ፡፡

 

ስለሌላ ጽሁፍ ደግሞ ትችቱን ነጥብ በነጥብ ከደረደረ በኃላ … እስካሁን የጻፍኩትን መለስ ብዮ ሳነበው . ሒትለር በዚህ ዓይነት ቅቤ አይደለም እንዴ! እያልክ የምታስቀኝ ትዝ አለኝ፡፡ እግረ መንገዱንም አንድ ታሪክ አስታወሰኝ ፡፡ እንዲህ የምል ነው፡፡ ….

 

ሰውዮው የወታደሮች አሰልጣኝ ነው ፡፡ ታዲያ የምስጋና ቃል ካፉ ይወጣል ማለት ዘበት ነው አሉ ፡፡ አንዱ እልክ የያዘው ምልምል ቀን ከሌት እየታተረ ሲዛጅ ከርሞ በፈተና ዕለት ዕጽብ ዱንቅ የተሰኘ ትርኢቱን ለአሰልጣኙ ያቀርባል ፡፡ አሰልጣኙ፣ እነደተኮሳተረ  ተመለከተውና ..ካንተም የከፋ አይቻለሁ ፡፡. ብሎ ሸኘው አሉ፡፤ ..በማለት አስቆኛል፡፤ መቼም አሰልጠኙ ራሱ ገደኛዮ እነደሆነ አርጋችሁ እንዳልገመታችሁ እርግጠኛ ነኝ ፡፡ ምክንያቱም ገደኛዮ አስተሳሰቡ እንጂ ዕድሜው ገና አንድ ፍሬ እምቦቃቅላ ነው ፡፡

 

እኔም አያርመኝም ትንሽ ነገር በጫርኩ ቁጥር ለሱ መስነበቤን አልተው እሱም መሳደቡን አይተው ነገሩ ደግነቱ በቃለት ሆነ አንጂ ቃላት ወደ ዱላነት የሚቀይሩ ቢሆን የምጸፍባቸው ጣቶች እርሳስም መያዝ ያቃታቸው ነበር የሆነ ነገር ጫጭሬ የሱን ሂስ ለመጫር ባገኘሁት አጋጣሚ እሞክራሁ ፡፡ ኦስካር ዋይልድ .. ሃስ ማለት ሻማ ነው፡፡ በሌሎች ለመለኩስ የሚጠብቅ ሻማ ..  አንዳለው የሱን የሂስ ሻማ ለመለኮስ ባለኝ ፍላጎት ሻማው ከተለኮሰ ግን በጣም ይቀጣጠላል ፡፡ ማረጋገጥ ከፈለጋችሁ የሆነ ነገር ጣጥፉና እባክህን ፈራችሁ ? አይዞን የሂስ በትርን እነሾክስፒር ሳይቀሩ ቀምሰዋለወ ፡፡ ለዚህም ሮበርት ሄንድሪክሰን ከላይ በተገለጸው መጽሀፉ ላይ ያቀናበረውን በዋቢነት እነሆ፡፡

 

ሼክስፒር ስድስት መስመሮች ያለስህተት አይጸፍም ሣሙኤል ጆንሰን፡፡

 

ቶማስ ባቢንባተን ማካውሌይ ስበር ትራንድ ባሬር ስራ ሲጽፍ፡- የትሮፒክ አየር ጸባይ ውስጥ ያልኖረ ሰው ነጎድጋድን አያውቅም የኒያጋራ ፋፋቴን ያላየ ደግሞ ስለፋፋቴ ትንሽ ቢያውቅ ነው ፡፡ የባሬን ማስታወሻ ያላነበበ ግን ውሸት ምን እንደሆነ አያውቅም ማለት ይቻል ይሆናል ፡፡ ብላል ፡፡

 

ማንነቱ ያልተዘገበ ሃያሲ የቶማስ ሃረዲን .. ያልታወቀችዋ ጁድ .. የሚለውን መጽሀፉን አቃጥሎ አመድን ልኮለታል ፡፡

 

ልምድ የሌለው ገጣሚ ደግሞ .. ለምንድን ነው የምኖረው ? ...በሚል ርዕስ ረዝም ግጥ ለኤውጌኔ ፊልድ / የመጽሄት አዘጋጅ / ልኮለት ፊልድ አንዳልተቀበለው ለማስረዳት.. የምትኖረው ግጥምህን በፐስታ ስለምትልክ ነው፡፡ ብሎ መልሶለታል ፡፡

 

ኦስካረ ዋይልድ እስር ቤት ውስጥ እያለ ማሩ ኮሬሊ / የብቀላ ደራሲ the one who’s forgotten / ጥሩ ጸሓፊ ስለመሆና ሲጠየቅ.. እንደ አጻጻፈ ከሆነ እስር ቡት መግባት ነበረባት፡፡ .. የሚል መልስ ሰጥታል ፡፡

 

ጌርትሩድ ስቴይን ሰውሻዋ ሔሚን ገ ዋይ ምስል አሸባሪ ሁን ፡፡ .. ስትል መክራለች፡፡ ሔሚን ግዋይ በስነጸሑፍ የቦሼክ ተሸላሚ ነበር ፡፡

 

ማርክ ትዌይን ለኔ የፓ ገጥም አይነበብም ልክ እንደ ጂን አውስቲን ፡፡ እንደውም ልዪነት አለ ፡፡ የፓን ግጥም ደመወዝ እየተከፈለኝ ባነበው እችላላሁ ፡፡የጂንን ግን በፍጹም ፡፡..

 

እስቲ በመጨረሻ ቲያትር አዘጋጁ ሃሮልድ ፒንተር የደረሰው ደብዳቤው የጻፈውን መልስ ላስነብባችሁና ልሰናበት ፡፡

 

ውድ …………..

. የልደት ቀን ግብዛ ስለሚለው ቲያትር አንዳንድ ያልገቡኝ ነጥቦች ስላሉ እንዲያብራሩልኝ በትህትና እጠይቃለሁ ፡፡

 

  1. ሁለቱ ሰዋች እነማን ናቸው ?
  2. ስታንሊ ከየት መጣ ?
  3. ሁሉም ግን ጤነኞች ናቸው ?

 

ለነኝህ ጥያቄዋች መልስ ካላገኘሁ ትያትርዋን ሙሉ በሙሉ ልረዳው አልችልም ፡፡

 

                                                የርስዋው ታማኝ

                                               ወ/ሮ ……………

ውድ ወ/ሮ …………………

የደብዳቤዋን ትርጉም ቢያስረዱኝ ያልገቡኝ ነጥቦች እነዚህ ቸናቸው ፡፡

 

  1. እርስዋ ማን ነዋት ?
  2. ከየት ነው የመጡት ?
  3. ጤነኛ ነዋት?

 

ለነኝህ ጥያቄዋች መልስ ካላገኘሁ ደብዳቤዋትን ሙሉ በሙሉ ልረዳው አልችልም ፡፡ 

            

 

                                                 የርስዋ ታማኝ ፡፡

                                                  ሃሮልድ ፒንተር

በሉ ደሞ እንግዲህ እርስዋ ከማንበብዋ በፊት ትችቱን ቢሰጠኝ ሃያሲው ጋደኛዬን ልፈልገው መቼም
0 Comment(s).

There are no comments to this entry.

Post New Comment

 BraveJournal Member Non-Member
No Smilies More Smilies »
Please type the letters you see