Powered by Bravenet Bravenet Blog

Tag Board

This tag board is currently empty.

Please type in the four characters shown in the black box.

Thursday, February 19th 2009

8:21 AM

Wedding

ጋብቻ

 

ጋብቻ በወንዶችና በሴቶች የሚፈጠር በህግና ማህበራዊ ኑሮ ደንብ የተደገፈ ጥምረት ሲሆን ከሁለቱም ወገን ለሚወለዱ ልጆች ኃላፊነት የሚያክልና በህግ ደንብ፣ ባህልና እምነት ተመረኮዘ የተጋቢዎችን መብትና ግዴታ የሚገልፅ ነው ይለዋል 16ኛው እትም ኢንሳይኮሎፒዲያ ብሪታኒካ፡፡

 

በ1962 ዓ.ም በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት የታተመው መጽሐፈ ህግጋት አብይት ደግሞ ጋብቻን ከሁለት አንዱ ዘር ለመተካት ልጅ ለመውለድ በሚገናኙበት ጊዜ ፈቃድን የሚሰጡበትና በዚህ ዓለም ድካምን ለማቅለል አንዱ ለአንዱ የሚያደርጉት በተጋቡት መካከል የሚደረግ መረዳዳት በማለት አስፍሮታል፡፡

 

ይህ የሚያመለክተን በዓለማችን በአብዛኛው ተቀባይነት ስላለው የአንድ ለአንድ ጋብቻ ነው፡፡

 በቦታ፣ በጊዜ አለፍ ሲልም በባህልና እምነት ልዩነት ምክንያት በምድራችን አስገራሚና ለጆሮ የሚቀፍ ግንኙነቶችና የጋብቻ ሥርዓቶች ተከናውነዋል፡፡ አልፎ አልፎም በተግባር ላይ እየዋሉ ናቸው፡፡ ከነኝህም ውስጥ ኢንሴስት (የቤተሰብ ውስጥ ወሲባዊ ግንኑነት)፣ ኤንዶ ጋሚ (የጎሳ ውስጥ ጋብቻ) ኤክሶ ጋሚ (ከጎሳ ውጪ ወይም ከጋብቻ ዝምድና ውጪ ያለ ጋብቻ፣ ፓሊጋሚ (የአንድ ለብዙ ጋብቻ) እ የተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ ይገኛሉ፡፡

 

ኢንሴስት የሚባለው ግንኙነት

በእናትና ወንድ ልጇ ወይም ደግሞ በአባትና ሴት ልጁ መካከል የሚደረግ ሲሆን ይህ ዓይነቱ ግንኙነት ወይም ጋብቻ በዓለም ደረጃ የተወገዘና የተከለከለ ነው የወንድምና እህት መጋባት ግን በማርሻልና ሃዋይ ደሴቶች በጥንታዊዋ አየር ላንድ በግብፅና በኢንካን ንጉሳዊ ቤተሰቦች ሲካሄድ ቆይቷል፡፡

ከቤተሰብ ወጣ በማለት ደግሞ ጋብቻ በአንድ ጎሳ ውስጥ የሚካሄድበት አጋጣሚ አለ ይህ ዓይነቱ በጥንት ጊዜ የታየ የጋብቻ ህግ ኋላ ቀር በሆኑ ከሌላ አካባቢ ጋር መገናኛ መንገዶች አስቸጋሪ በሚሆንበት ጊዜም ሆነ በየአካባቢው ካለ የባህል ተጽዕኖ አሁንም ሲተገበር ይስተዋላል፡፡ በእንግሊዘኛ ቋንቋም ኤንዶጋሚ ተብሎ ይታወቃል፤፤

ከዚህ በተቃራኒ ያለው ኤክሶጋሚ የሚባለው ሲሆን ጋብቻው የሚፈፀመው በተጋቢዎች የዘር አቆጣጠር በመመርኮዝ ነው፡፡ ይህ የጋብቻ ዓይነት በዘመኑ ሁኔታ ተሻሽሎ እየተሰራበት አለ ለምሳሌም በእንግሊዝ አገር ለሁለተኛ ጊዜ የሚያገባው ሰው የባለቤቱን እህት ወይም ወንድም እንዲያገባ ሕግ ይከለክለዋል፡፡

 

በኛም መጽሐፍ አብይት ህግጋት ከሥጋ ዘመዶች ጋብቻ ሌላ በጥምቀት ክርስትና ዝምድና የተሳሰሩትን ሳይቀር እንዲጋቡ አይፈቅድም፡፡

ከተፈጥሮ ህግ ውጪ አንድ ዓይነት ፆታዎች ከህግ ተደብቀው ጋብቻን የፈጸሙ ተከስተዋል እነኝህም እንደዚሁ በዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ተወገዙና የተጠሉ ናቸው፡፡

ከነዚህም ሌላ በ20ኛው ክፍለ ዘመን እየቀነሰ የመጣው የአንድ ለብዙ ጋብቻ ወይም

ፓሊጋሚ የሚባለው ነው፡፡ ፓሊጋሚ በእስልምና ሃይማኖት ህግጋት ታሪክ የአንድ ለብዙ ጋብቻ ተፈቅዷል፡፡ አሁንም በአንድ የአፍሪካ ማህበረሰቦች ይህ ዓይነቱ ጋብቻ ይፈፀማል፡፡ የአንድ ለአንድ ጋብቻም በአብዛኛው እያሰረፀ በመምጣቱ ፓሊጋሚ አልፎ አልፎ ብቻ ነው የሚታየው ይህ ጋብቻ ምርታማነትን በል ልዩ መንገድ የሚቀንስ ከመሆኑም ሌላ የቤተሰብ አባላት ቁጥር ከቤተሰብ ቁሳዊ ምርት እንዲበልጥ የሚያደርግ በመሆኑ የህዝብ ቁጥር ዕድገትን አስቸጋሪ ከሚያደርጉት ነገሮች እንደ አንዱ ሊቆጠር ይችላል፡፡

የፖሊጋሚ ነገር ሲነሳ በዘመናችን ጉድ ተሰኘው ቶም ግሪን ይጠቀሳል ቶም ግሪን አምስት ሚስቶች ሲያገባ በግንቦት 11 1983 አዲስ ዘመን ጋዜጣ አድማስ አምድ ያሰፈረው “ከህብረተሰቡ ወግ ባህልና ልማድ አፈንግጦ እንዲሁም ክልክሉንና ውግዙን የቤተዘመድ የእርስ በርስ ጋብቻ ህግ ሽሮ የእንጀራ ልጆች ከነእናት ስለማግባቱ የሰማም ሆነ ያወቀ አልነበረም›› በማለት ነበር፡፡

 

በመጨረሻም በዘመናችን ውስጥ ተቀባይነት ስላለው የአንድ ለአንድ ጋብቻ ትንሽ ልበል፡፡ የትዳር ምስረታ በተለያየ ቦታ ባለው የኢኮኖሚ ማህበራዊና ባህላዊ ሁኔታ ቢወሰንም የእድሜ ደረጃም ግምት ውስጥ ይገባል፡፡

 ቱኒዝያ ቤተሰብን በእቅድ ለመምራት እንዲያስችላት የአንድ ለብዙ ጋብቻን አስቀርታ የጋብቻን እድሜ ለሴቶች 17 ለወንዶች ደግሞ 21 ዓመት እንዲሆን ወስናለች ይላል የህዝብ ቁጥር እድገትና የልማት ጥያቄ በሚል ርዕስ ይዞ ያወጣው መስከረም ቅጽ 9 ቁጥር 35 በ1981 እትሙ፡፡

ጋብቻ ሙሉ በሙሉ ነፃ ምርጫ ነው ለማለት ያስቸግራል፡፡ በሰለጠነው ኣለም ፍቅር ከጋብቻ ጋር እየተያያዘ ቢመጣም ለዘመናት ፍቅር ለጋብቻ የሚያንደረድር ሆኖ አልተገኘም፡፡ ለፍቅር ከዚያም ለጋብቻ በሚታጩት ላይ ማህበረሰቡ ትኩረት ያደርግባቸዋል ወንዱ ለጋብቻ የፈቀዳትን (በፍቅር ተዋውቀውም ቢሆንም ለቤተሰቦቿ ሽማግሌ ልኮ ስምምነት ሲጠይቅ የልጅቷ ቤተሰቦችም የሚያጣሩትን አጣርተው እስኪፈቅዱ መቆየትም ነፃ ምርጫ አለመሆኑን ያመለክታል፡፡

 

በእንግሊዝ አገር ያለው የጋብቻ ህግ ለጋብቻ አስፈላጊ የሆኑትን ጉዳዮች እንደሚከተለው ተንትኖታል፡፡

-       እያንዳንዲ ወገን ለጋብቻ የደረሰ መሆኑ

-       ለወሲባዊ ተራክቦ ብቻ የሆነና ህመም የሌለበት

-       በዘር ሃረግ ውስጥ ዝምድና አንዳቸው ከሌላቸው ከተረጋገጠ እና በሚመለከተው መስሪያ ቤት የጋብቻው ስርዓት ሲፈፀም ነው፡፡

 

አውሮፓ ውስጥ ባሉት ማህበረሰቦችና በአሜሪካ ያለው የጋብቻ ህግ (በእንግሊዝ የጋብቻ ህግ ላይ የተመሰረተው) የሮማውያን፣ የካቶሊክ ካኖን ህግ ውጤት ሲሆን በዘመኑ የኢንዱስትሪ ከተሞች ህይወት ማህበራዊና ባህላዊ ሁኔታዎች አኳያ ተሻሽሎ የተቀረፀ ነው፡፡

 

በቀድሞው ሰብየት ህብረት የሲቪል (ህዝባዊ ጋብቻ በሚመለከተው ክፍል ሲመዘገብ ብቻደ ነው፡፡ ዕውቅናን የሚያገኘው አሁን በየሪፐብሊኩ ባህል ካልተለወጠ የአንድ ለአንድ ጋብቻ በጠበቀ መልክ ይከናወናል፡፡ ጋብቻውም በሁለቱም ወገን በፈቃደኝነት ላይ የተመረኮዘና ተጋቢዎቹም ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ መሆን አለበት፡፡

 

   በጃፓን ጋብቻ ከመከናወኑ በፊት ወንዶች 18 ዓመት ሴቶች ደግሞ 16 ዓመት ሊሞላቸው ይገባል፡፡ ጋብቻ በህግ መደገፍም ተገቢ ነው በቻይናም ጋብቻ በህግ ይፀድቃል፡፡

   በሀገራችን ጋብቻ በሶስት ዓይት መንገድ ሲታወቅ እነሱም በማዘጋጃ ቤት የሚመዘገብ ህዝባዊ ጋብቻ በቤተክርስቲያን የሚከናወን የሃይማኖት ጋብቻና በተለይ በየገጠሩ የሚከናወኑ ባህላዊ ጋብቻዎች ናቸው፡፡

   ስለጋብቻ ይህን ያህል ካልኩ እስቲ ደግሞ በአንድ ወቅት በአዲስ ዘመን የአድማስ እትም ላይ ወጥቶ የነበረውን ልጋብዛችሁና ልሰናበት

 

የጋብቻ በዓላት

በጋብቻ ታሪክ ውስጥ አብሮ በመኖር ከባልና ሚስቶች ሁሉ የበላይነቱን የያዙት ለሩሲያውያኖች ቲሙልጅና ወይዘሮ ሮእማን ናቸው 87 ዓመታት አብረው ኖረዋል፡፡

ፈረንጆች የየዓመቱን የጋብቻ በዓለም እየሰየሙ ደለድለውታል ባልና ሚስቶች ተጋብተው አንድ ዓመት ሲሞላቸው የሚያከብሩት የጋብቻ በዓል የወረቀት ይባላል፡፡

 

2ኛው       የጥጥ                10ኛው      የቆርቆሮ

3ኛው       የቆዳ                11ኛው      የጠንካራ ብረት

4ኛው       የላይነን                   12ኛው      የሐገር

5ኛው       የዕንጨት              13ኛው      የጠፍር (የገመድ)

6ኛው       የብረት              14ኛው      የዝሆን ጥርስ

7ኛው       የሲቻ (የነሐስ)         15ኛው      የክሪስታል

8ኛው       የመዳብ               25ኛው      የብር

9ኛው       የሸክላ                    50ኛው      የወርቅ

                             60ኛው      የአልማዝ

 


ማስታወሻ

 

     ከትዳር በፊት ቀዳሚ ሁኔታዎች አሉ፡፡ መተዋወቅ፣ የእረፍት ጊዜን አብሮ ማሳለፍ፣ መጠናናት እና መተጫጨትን የመሰሉ ሂደቶች ይከናወናሉ፤፤ ሽማግሌ መላክ፣ ደጅ መጥናትና ወይም የጨዋ በር ድሮም የሚቆምበት ነው በሚለው ባህላዊ አነጋገር በመንተራስ ደጅ ማስጠናትም አለ፡፡ ከዚህ ውጣ ውረድም በኋላ ትዳር ይመሰረታል፡፡ የማህበረሰብ መሠረት፣ የቤተሰብ ጣራና ግድግዳ ቆመ ማለት ነው፡፡

     ማህበረሰብ የተለያዩ ቤተሰቦች በማሰብ በመሆኑም ጤነኛ ቤተሰብ በመልካም ምግባር የታነፀ ልጆችን ያፈራል፡፡ እነዚህም ልጆች አድገው በማህበረሰቡ ውስጥ ቦታቸውን በመያዝ የባህልን ህግጋቶች በማክበር የራሳቸውን ቤተሰብ ሲመሰርቱ ለማህበረሰቡ እልፍ ብሎም ለሀገር አለኝታ ይሆናሉ፡፡

     አንድ ቤተሰብ ፍቅር ከሌለበት ልጆችም ባህርያቸው ፍቅር የጎደለውና የማህበረሰቡን ህግጋቶች ሳያከብሩ በአብዛኛው ዋልጌዎች ፍቅር የጎደለውና የማህበረሰቡን ህግጋቶች ሳያከብሩ በአብዛኛው ዋልጌዎች ሆነው ይቀራሉ፡፡ በአሳፋሪ ተግባሮችም ይሰማራሉ፡፡ በዚህም ለማህበራዊ ችግሮች መባባስ እንደ አንድ ምክንያት ሆነው ይወስዳሉ፡፡

     እንግዲህ የአንድ ቤተሰብ ጣሪያና ግድግዳን የሚያዋቅሩት ባልና ሚስት ስለሆኑ (በትዳር ለመቆየት) በሚለው መጽሃፉዋ ጂሊ ኩፐር ብዙ ብላለችና እሷን ልጋብዛችሁ፡፡

     በትዳር ላይ ያለዎ አመለካከት ምን ያህል ጥሩ እንደሆነ እንዲረዳደዎም በዘመናዊ ስነልቦና ዘዴዎች ተቀነባበሩ ጥያቄዎችን በዊሊያም በርናርድና ጁልስ ልዎፖልድ ከተዘጋጀው እራስዎን ይፈትኑ መጽሐፍ ውስጥ ትዳርን የሚመለከተውን ብቻ ወደ አማርኛ መልሼ አቅርቤላችኋለሁ፡፡ ለጥያቄዎቹም መልስ ከመጽሐፉ በስተመጨረሻ ያገኙታል፡፡

 

መልካም የንባብ ጊዜ

 

ተርጓሚው

 

   ጋብቻ ጤንነት ነው ምን ያህል ሊከበር እንደሚገባው የምትረዱት ትዳራችሁ ከፈረሰ በኋላ ይሆናል፡፡ በትዳር ዓለም መቆየት ሁሉም ተጋቢዎች ቁጥራቸው እየበረከተ የመጣው ትዳር አፍራሾች እንደሚያውቁት ችግር ነው፡፡

          ጂሊ ኩፐር ለሁሉም ችግሮች የሚሆን መፍትሔ በርግጥ የላትም ነገር ግን ለእንያንዳንዶቹ ማለትም የማር ጨረቃን እንዴት ማዘጋጀት ይቻላል? ቅናትን መቋቋሚያና መንገዶች ታማኝ ስላልሆነ አፍቃሪ በገንዘብ ጉዳይ የሚገጥሙንን ግጭቶች ንትርኮችን ማስወገጃ ዘዴዎችን በአልጋ ውስጥ በበዓል ቀናት ግብዣ ላይ ፀባያችን ምን ይምሰል አላስፈላጊ እንግዶችን ለመሸኘት አለሌነትን ስልቹነት እንዲሁም የተለያ ፍላጎቶችን ማረቂያ ብልሃቶችን ፍጥምጥም ለፈፀሙ ጓደኛሞች ለአዲስ ተጋቢዎችና ፍቺን ለሚስቡ ሁሉ የሚሆኑ በጣም ጥሩ ምክሮች አላት፡፡

     በቅድሚያ ልታውቁት የሚያስፈልገው እዚህ መጽሐፍ ውስጥ ከተጠቀሱት ችግሮ ች አንዳንዶቹ ወይንም ወደፊት ሊገጥሟቸው እንደሚችሉ ነው፡፡

 

 


ማውጫ

 

-       መግቢያ

-       ሙሽራዋ

-       የማር ጨረቃ

-       ቤትን ማደራጀት

-       ቤትን ማስተዳደር

-       በትዳር ሕይወቴ ልቋቋመው የማልችለው አንድ ነገር

-       ንትርክ

-       በእንሰቶች በኩል ስላሉ ችግሮች ማስታወሻ

-       የገና በዓል

-       ዘመዶች እና ጓደኞች

-       የመዝናኛ ሃሳብ

-       ቢሮ

-       አጠቃላይ የትዳር ችግሮች /እንከኖች/

-       ልብስ

-       በዓላት /የበኣል ቀናት/

-       ግብረ ስጋ /ወሲብ/

-       የከዕለታት አንድ ቀን ጓደኝነት

-       ከምሪት ነፃ መሆን

-       የልጆች መወለድ

-       መደምደሚያ


መግቢያ

 

ጋብቻ መፈፀም ከመጠን በላይ ቀላል ነው ፈቃዱን ለማግኘትም እንዲሁ በጣም አስቸጋሪ የሚሆነው ግን በጋብቻ ለመቆየት ነው፡፡

     በዚህ ርዕስ ላይ መፅሀፍ የተዳፈርኩበት ምክንያት የእናትና አባቴ ደስታ የሞላው የ40 ዓመት የጋብቻ ጊዜንና የራሴን የ8 ዓመት ውድ ትዳሬን እንደምሳሌ በመውሰድ ነው፡፡ በ8 ኣመታት ውስጥ በጣም ውብ ሆኑ ጊዜያቶች ገና እንዲሁም ትዳራችንን ከሥር መሠረቱ ሊገነድሱት የተቃረቡ መጥፎ ሁኔታዎች ነበሩ፡፡ ነገር ግን በነዚህ መጥፎ ወቅቶች በትዕግስት መቆየት ትዳራችሁ ከመፍረስ ድኖ ይጠናከራል፡፡

     ብዙዎቹ ጓደኞች ትዳር ዓለም ገብተዋል፡፡ ከትዳር ዓለም ወጥተዋል፡፡ ነግር ግን በዚህ ርእስ መፃፍ መጀመሬ ስለተሰማ ጓደኞቼ ቤት ስሄድ ምንም እንዳልተፈጠረ ሆነው ስለሚቀርቡኝ የመጻፍ ግዴታዬን ለማሟላት ከበድ ያለ ችግር ገጥሞኛል፡፡ እናም የሌሎች ሰዎች ጋብቻ ያልታወቀ ድቅድቅ ጨለማ ነው፡፡

     ለኔ ጋብቻ አመቺ ሁኔታን ከፈጠሩት አንዱ ምክንት ባሌ አግብቶ የፈታ ስለነበረ ነው፡፡ በሚገኝሙኝ መጥፎ ጊዜያቶች ውስጥ ሻንጣዬን ይዤ ልወጣ ስል ባሌ በጋብቻ ውስጥ እንዲህ ዓይነት ነገሮች እንደሚጠብቁ እሱም ለመጀመሪያ ጊዜ ሲያጋጥመው ከኔ ይበልጥ እንደተማረረ እያለሳለሰ ያረጋጋኝ ነበር፡፡

     እናም በትዳራችን ላይ ያንዣበቡትን አደጋዎችና ችገሮችን እንዴትም እንዳለፍናቸው መጠቀም ጋብቻ ለሚያስቡና በትዳር ላይም ሳሉ ለደህና ሕይወት ያዘጋጃቸዋል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡


ሙሽራዋ

ሠርግ

          ይህ ቀን አንቺ /ወይንም እናትሽ/ ሕይወታችሁን ሙሉ የምትጠብቁት ነው፤፡ እንደ ሕልም/ ዋላ/ ያልፋል፡፡ ከዚያም አንድም ነገር ልታስታውሱ አትችሉም፡፡  እድምተኞች ጋር ስትወጡ ትንሽ ሞቅ ባላችሁ ጥሩ ነው፡፡ ግን አታብዙ ጫማችሁ ላይ የተንጠለጠለውን የዋጋ ፅሁፍ ከጫማው ላይ ማንሳታችሁን ኣረጋግጡ ቤተክርስቲያን ውስጥ ስትንበረከኩ ይታያልና፡፡

     ሙሽሪቶች ዝንጥ ባትሉም አትከፉ አለያ በእንቅልፍ ማጣት ዓይናችሁ አብጦ የአሳማ ዓይን እንዳይመስልና እንዳያሳጣችሁ፡፡

     ሙሽራዋ ደረጃውን እየወረደች ወዳንተ ስትመጣ በፈገግታ ልትመለከታት እንደሚገባህ አትርሳ፡፡ እሷ አበባ ታቅፋ ብታቀረቅርና ልታይህ ባትችልም ዙሪያውን የከበበህ እድምተኛ ይመለከትሃል፡፤

     ከቤተክርስቲያኑ ደረጃ መውረድ አስቸጋሪ ነው፡፡ የት እንደምትመለከት ግራ ይገባሃል ያ የሚያንፀባርቅ ፈገግታህ ሹፈት የተሞላበት ፈገግታ የያዘው ልታየው የማትፈልገውን ሰው ዓይተህ ሊለወጥብህ ይችላል፡፡

     ሃሳብ የገባህ ከመሰልክ ሰዎች ጋብቻህን በእርግጥ መፈለግህን እንደገና እያመዛዘንክ እንደሆነ አርገው ያስቡታል ጥሩ መመሪያ የሚሆነው ቀዝቀዝ ያለ ፈገግታ ለብሰህ የቤተክርስቲያኑን በር መመልከት ይሻልኃል፡፡

     በስርዓቱ ላይ የሚመረጠው ዜማ ላይ ጥንቃቄ አድርግ ሰዎች በሰርግ ላይ ልብ ሚሰረስር ቆንጆ ዜማ ይሰዳሉ፡፡ ስለዚህ ምርጫህ አስቀያሚ እንዳይሆን ተጠንቀቅ አሻሚ ትርጉም ያላቸው ዓይነት ከመምረጥም ተጠንቀቅ የሰርጉን ሥነ ሥርዓትና ክብር የሁሉም ሰው ሳቅ እንዳያበላሽብህ፡፡

 

መስተንግዶ

     እንደ ቅቤ የሚያንፀባርቅ ፈገግታ ተላብሰው በተርታ የቀሙትን ሰዎች ሲጨብጡና ፊታቸውን ለማስታወስ ሰውነቱ በጣም ሊደክሙ ይችላሉ፡፡ ለንጉሳዊያን ቤተሰቦች /የሁል ጊዜ ሥራቸው ስለሆነ/ ሀዘኔታ ሳይሰማዎት ይቀራል፡፡

     በእንግዶች መሀል ስትዘዋወሩ አንዳቸውም ባያነጋግሯችሁ ሃሳብ አይግባችሁ ሁሉም የሚያስቡት እናንተ በጣም አስፈላጊ ስለሆናችሁ ከነሱ ጋር በማውራት ጊዜያችሁን ማጥፋት እንደሌለባችሁ ነው፡፡

     ንግግር ማድረግ ካለባችሁ አጠር አድርጉት በአካባቢያችሁ ላሉት ሁሉ ምሥጋና አቅርቡ፡፡ አማቻችሁ የቀልድ ለዛ እንዳላችው አድርገው እንዲያስቡም አንድ ጥሩ ቀልድ ጣል አድርጎ ሚዜያችሁ ንግግር እንድያደርግ ወይም ቴሌግራም እንዲያነብ አትፍቀዱ፡፡

     ከድሮ ጓደኞቻችሁ ጋር አትሳፈጡ እንዲት የማውቃት ልጅ ባሏ በመስተንግዶው ላይ የድሮ የሴት ጓደኛውን አግኝቶ ታስታውሻለሽ ብሎ ጨዋታ ስለጀመረ ሙሽሪት ማር ጨረቃ ጉዞዋን ሰርዛለች፡፡

     ላለመስከር ሞክሩ ስካሩን ብትፈልጉትም በኋላ ሊረብሻችሁ ይችላል፡፤

 

የማር ጨረቃ

     ከሥር መሰረቱ የማር ጨረቃ ባሎች የዋህና ንፁህን ሙሽሪቶቻቸው ለወሲባዊ ፊንጠዚያና ምስጢር የሚያነሳሱበት ጊዜ ተብሎ የተወጠነ ነበር፡፡ በአሁኑ ጊዜ ብዙዎቹ ተጓዳኞች ከጋብቻ በፊት ወሲብ የጀመሩና ቤት በመስራት የከሰሩ እናም ሁሉም ነገር የተበለሻሸና አላአስፈላጊ ወጪ ይመስላቸዋል፡፡ ተጓዳኞች ሁላችሁም ግን የበኣል ቀን ያሥፈልጋችኋል፡፡

     መድረሻ ላይ ስትቀርቡ ትልቁን ደስታችሁን የሚረብሽ ስሜት ሊሰማችሁ ይችላል፡፡ በሰርጉ ላይ በጠጣችሁት መጠጥና ባሳለፋችሁት ውክቢያ በጣም ደክማችኋል፤፡

     ለወራት ያህል ከሰርግ አዘጋጆች ጋር ከሚዜዎች ስለሚዜ ልብሳቸው በየቀኑ ስለሚደርሱት እሸጎች ከልብስ ሰፊዎች ጋር በነበረው ጭቅጭቅ እያንዳንዱ ደቂቃ ተጣባ በመጨረሻ ሁሉም ነገር አልቆ ባልና ሚስት ሌሊቱን ብቻችሁን ትቀራላችሁ፡፡

     ለሙሽሪት በተለይ በድንገት ሁሉም ነገር አዲስና ያልተለመደ ነው፡፡ ሻንጣዋ የዕጅ ቦርሳዋ አዳዲስ ልብሶቿ አንፀባራቂው ነው የውስጥ ልብሷ ከሰለቻት ይልቅ ስሟም ሳይቀር በውጪ አገር በሚደረግ ጋብቻ የቤተሰቦቿን ትታ በባለቤቷ ስለምትጠቀም አዲስ ነው፡፡

     ማስታወሻ የሚገባን ነገር ቢኖር ሚስቶች /ባሎቿን/ ምናልባት ልክ ጫካ ውስጥ እንደነበሩና ሁልጊዜ በጣም እንደሚፈሩ አውሬዎች በማሰብ ሲፈሩ መረጋጋት ሊያስፈልጋቸው ይቻል ይሆናል፡፡

    

ሰቦረትስ /ተንኮለኞች/

     ለማር ቸረቃችሁ እንዲሆን የወሰናችሁበት ሆቴል ስትደርሱ መኝታ ቤታችሁ ተንኮል ሥራ ወጥመድ እንዳይኖረው ፈትሹ/ በፈረንጅ አገር የሚሰራበት ነው/ ቀልደኞች የሰርሁ እድምተኞች ምናልባት የሆቴሉን ስታፍ ቀድመው በማነጋገር የረገበ አልጋ ያለበት ክፍል ወይንም አልጋው ከእሳት አደጋ የጥሪ ደወል ጋር ተያያዘበት ክፍል ሊያሰጧችሁ ያስባ፡፡

     እኔ የማውቃቸው ተጓዳኞች ቦታ ያስይዙበት ሆቴል እንደደረሱ የሆቴሉ ሥራ አስኪያጅ ከአንድ ቀልዶች የተላከ ቴሌግራም አስነብባቸዋለሁ እንዲህ የሚል ባለቤቴ ከቅርብ ጓደኛዬ ጋር ከጥቂት ጊዜ በፊት ኮብልላለች፡፡ አቶ                 እና ወ/ሮ                  በሚል ሽፋን እናንተ ሆቴል ክፍል እንደያዙ አምናለሁ እኛ እስክንመጣ ድረስ የተያዘውን ከፍል እባካችሁ እንዳትሰጧቸው? የማር ጨረቃን ለማሳለፍ ወደ ባሐማስም ይሁን ቤሊዝ ብትሄዱ ተንኮለኞችን ለማሳት መድረሻችሁን አለመናገሩ ይጠቅማል በቀላሉ ለሁሉም ሰው ሸራተን ሆቴል እንደምትቆዩ ነግራችሁ ሒልተን ቦታችሁን ያዙ፡፡

     ከዚያም አብሮ መኖሩን ለመልመድ ችግር ማጋጠሙ አይቀርም ሚስት በተለይ መልኳን ለመጠበቅ ትጨነቃለች ከጋብቻ በፊት ማታ ምግብ ቅባት መጠቀም ለምዳ ይሆናል አሁን ግን ባሏ ለሁልጊዜውም አብሯት ስላለ ሚስጥሯ ሊጋለጥ ነው እግሯ ላይ ያለውንስ ፀጉር መቼ ትላጨዋለች? ለባሏ ፀጉሯ ቡና ቀለም የተፈጥሮ እንደሆነ ነግራው ነበር እናም በድንገት ፀጉር መቅለሚያዋን ሻንጣዋ ውስጥ ሊያገኘው ነው፡፡

     ልክ ባሏ ገላውን ሲታጠብ ፀጉሯን እየላገች ማውራቷን እንደምትለምደው ሁሉ ሁሉንም ነገር በፍጥነት ትለምደዋለች፡፡ ወይንም ባኞ ውስጥ ልብስ እንደመቀየር ፈንታ ቤቷ ውስጥ ራቁቷን መዞሩን፡፡ በትናንሽ ጡቶቿ የምታፍር ቢሆን እሱም በጸጉር አልባ ደረቱ በእኩል ደረጃ ይሰማው ይሆናል፡፡

 

በማግስቱ ጠዋት

     ጠዋት የመኪና ግጭት የደረሰብኝ እመስላለሁ የሚል ጭንቀት ያደረብዎት ከሆነ መጋረጃውን ዘግተው ይተኙ እናም ኣፍዎ የፖሮት /ተናጋሪ ወፍ/ ጎጆን ሽታ ያሸትብኛል ብለው ካሰቡ ባልዎ ሊስምዎ ጠጋ ሲል ሽንት ቤት መሁድ እንደሚፈልጉ ያስቡና ጥርስዎን ያጽዱት፡፡

     ቢሰለችዎ ጭቅጭቅ ቢያጋጥምዎ የታፈኑ ከመሰለዎና ቤተሰቦችዎ ከናፈቁዎ አይደናገጡ እነኝህ ሁሉ አብረው ያደጉ ሕመሞች ናቸው፤፤ ሕመሞቹ ለሚቀጥሉት 50 ኣመታት የባህርይ መስተካከል ስ

0 Comment(s).

There are no comments to this entry.

Post New Comment

 BraveJournal Member Non-Member
No Smilies More Smilies »
Please type the letters you see