Powered by Bravenet Bravenet Blog

Tag Board

This tag board is currently empty.

Please type in the four characters shown in the black box.

Tuesday, February 24th 2009

5:14 AM

jimi

      የጂሚ ሄንድሪክስ አሟሟት እንደገና መጣራት ጀመረ

   አነቃቂ እጽ ከመጠን በላይ በመውሰድ ህይወቱ ሊያልፍ ችሏል ተብሎ ከዛሬ 24 ዓመት በፊት ምርመራው የተዘጋበት የእውቁ ሮክ ጊታር ተጫዋች የጂሚ ሔንድሪክስ አሟሟትን እንደገና ለማጣራት መጀመሩን ለንደን የሚገኘው የእስኮት ላንድ ያርድ ፖሊስ አስታውቋል ፡፡

  የቀቃቤ ህጉ ቢሮ ስለ ሁኔታው ሲያብራራ ይህን ጉዳይ እንደገና ለመመርመር መነሻ የሆነው ማንነቱ ሊጠቀስ ያልተፈለገ አንድ ሰው መሆኑን ገልፆል፡፡

   እ.ኤ.አ. በ1942 ሲያትል ውስጥ የተወለደው ጂም ሔንድ ሪክስ ለስራ ሐላፊው ቻስ ቻንድለር እርዳታ በጣም ያስፈልገኛል የሚል መልእክት ትቶ ነበር መስከረም 18 ቀን 1970 ዓ.ም በለንደን ውስጥ ህይወቱ ያለፈው ፡

    አንድ የህክምና ሰው ምርመራውን ሲያጠቃልል ሄንድሪክስ ከመጠን ያለፈ አነቃቂ ዕፅና አልኮል ከመውሰዱ በኃላ ታፍኖ መሞቱን በማተት ነበር፡፡

   ‹‹  ስኮትላንድ ያርድ የፖሊስ ክፍል የጂሚ ሄንድሪስ አሟሟት ሁኔታ እንደገና ጥናት እንዲያደርግበት በእንግሊዝ መንግስት ፍርድ ቤት ተጠይቋል የማጣራቱ ተግባር ምን ያህል ጊዜ እንዲፈጅ አሁን ባይታወቅም አጠቃላይ ሪፖርቱ ግን ለፍርድ ቤቱ ይቀርባል፡፡ በማለት የስኮት ላንድ ያርድ አፈ ቀላጤ ካርል ቤዊክ ቃሏን ሰትታለች፡፡

   ‹‹ ዴይሊ መቷል ›› ጋዜጣ ደግሞ በበኩሉ በጂሚ አሟሟት እንዲጣራ ጥያቄው የቀረበው ካቲ ኤቺንግሃም ከተባለች የቀድሞ የጂሚ ጓደኛ ሲሆን የግል የምርመራ አጣሪ ቡድኖች ኮሚሽን እንደከፈለች ዘግቧል፡፡

    ሚስ ሌግንቺሃም ለጋዜጣው አሟሟቱ ምንም የማይመስል ነው መሆን በነረበት ብዬም አላስብም በመጥፎ ቦታ ትክክለኛ ባልሆነ ግዜና ትክክለኛ ካልሆኑ ሰዎች ጋር ነበር ጂሚ የተገኘው ስትል ተናግራለች

    ከእድሜና ሙያ ጓደኞቹ እጅግ ልዩው ያሮክ ጊታር ተጫዋቹ በዚያን ወቅት የ27 ዓመት ወጣት ነበር ፡፡ ህይወቱ አልፎ የተገኘውም የቀድሞዋ የበረዶ ሸርተቴ ሻምፒዩኗና የሱ የሴት ጓደኛ ከሆነችው ሞኒካ ዳንማን አፓርታማ ውስጥ ነው፡፡

 

  የጂሚ እንድሪስ ኤክስፕሪያንስ የሚል መጠርያ ባለው ባንድ ውስጥ የቤዝ ተጨዋቹ ኖኤል ሬዲንግ ደግሞ ለቢቢሲ ራዲዮ 4 ሲናገር አሟሟቱን ስሰማ በጣም ነበር የደነገጥኩት ፍጹም ያልጠበኩት ነበር አነቃቂ እጽ እንወስዳለን ግን በዛ ካለ እጽጋር  አንድ ጠርሙስ ቢኖ ማንኛችንም ቢሆን አናደርገውም ብሏል፡፡ ሌዲንግ የጓደኛው አሟሟት ላይ ስለተደመጡት ጉዳዩች ሁልግዜም ጥርጣሬ እንዳለው ነው፡፤

  ከሁለት አመት በፊት ነበር በወቅቱ የነበሩት የአንቡላንስ ሰራተኞች ከአሉበት ተፈልገው ቃላቸውን እንደሰጡ እነርሱ ለእርዳታ በደረሱበት ወቅት ጂሚን ብቻውን እንዳገኙ የተናገሩት ይህ ሁኔታ ደግሞ በጊዜው ከጂሚ ጋር እንደነበረ ቃሉን የሰጠው ከሰው ጋር ይጋጫል እንግዲህ አንቡላንሱ ከመድረሱ በፊት የጂሚ ህይወት አልፎል እናም ማንም ይሁን ማን ሁኔታውን ለመሸፋፈን ጥረት አድርጓል፡፡

  ጂሚ ሔንድሪክስ በህይወት በነበረበት ግዜ አምስት የሙዚቃ አልበሞችን ሰርቶ አውጥቷል ይህን ሞት ያለግዜው የቀደመውን ተሰጥኦ አፍቃሪ ለሆኑት አድማጮቹ እሱ ካለፈ በኃላ 300 ያህል የሙዚቃ ስራዎቹ ተቀርጸው በገበያ ላይ ውለዋል፡፡

  ሄንድሪስ 1960ዎቹን በልዩ ስልቱና እጅግ አስገራሚ ቴክኒካዊ ችሎታው ድንቅ ስራዎቹን አስመስክሮባቸዋል፡፡ በመድረክ ላይ ያሳይ የነበረው ለየት ያለ እንቅስቃሴው ጊታሩን በጥርሱ ከመጫወት ጋር ሄዶ ጀት የተሰኘው ዘፈኑ በ1967 እጅግ ዝነኛ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ ይህ ዝናው የተትረፈረፈው በአካል ቀርቦ ከሚጫወትባቸው የመድረክ ጨዋታዎችቹ የመነጨ ሲሆን በአንድ ወቅት የሚያሙን ጦርነት በመቃወም የአሜሪካንን ህዝብ መዝሙር ድብልቅልቁ በወጣ ፍንዳታ መሰል ሙዚቃ ቅንብር በውድስት ቶክ ማቅረቡም የሚጠቀስ ነው ሌላው በዋይት አይስል ለ250.000 ተመልካቾች ዝግጅቱን ማቅረቡ እና በሞንተሬይም በተመልካች ፊት ጊታሩን በእሳት ማቃጠሉ ጉድ የተሰኙ የህይወቱ አብይ ግዜያት ሆነው ይታወሳሉ፡፡

     

 

0 Comment(s).

There are no comments to this entry.

Post New Comment

 BraveJournal Member Non-Member
No Smilies More Smilies »
Please type the letters you see