Powered by Bravenet Bravenet Blog

Tag Board

This tag board is currently empty.

Please type in the four characters shown in the black box.

Tuesday, February 24th 2009

5:16 AM

የፊልም አዘጋጆች

የፊልም አዘጋጆች 

  የሮኪ ክፍል 5 አዘጋጅ ጆን አቨልድሰን ልክ ሲልቭር ስታሎን እንደፈለገው ሁሉ የሮኪን መጨረሻ ሞት ሊያደርገው አስቦ ነበር ፡፡ ጆን አፊልድሰን የሮኪ ምት ላይ ፊልሙ ቢጨርስ በጣም ጥሩ ይሆን እንደ ነበር ገምቷል፡፡ ነገር ግን እስታሎን በፈለገው መንገድ ተከራክሮ ስላልተሳካለት እሱም ለመሞከር አልዳዳውም፡፡

  የፊልም አዘጋጅነት ሙያ እንደታወቀው አጠቃልይ የቀረፃ እንቅስቃሴዎችን የመቆጣጠርና የማስተባበር ጥበብ ቢሆንም በሆሊውድ አካባቢ ይህ ስልጣን ያላቸው የፊልም አዘጋጆች በጣት የሚቆጠሩ ናቸው፡፡ ባለገንዘብ የሆኑት የፊልም አዘጋጆች በገንዘባቸው ስለሚያዙበት ያሰቡትን እና ያቀዱትን ለመስራት ይችላሉ፡፡

  ለምሳሌ ስቲቨን ስፒልበርግ የተባለው ዝነኛ የፈልም አዘጋጅ ጃውስ ( 1975 ) ኤክስትራ ቴሬስትያል ( 1982 ) የኢንድያን እና ጆንስ ተከታታይ ፊልሞች ( 1981-1989 ) እና ጁራሲን ፓርክ በተሰኙት ፊልሞች ይታወቃል፡፡ ከነዚህ ፊልሞች ካገኘው ገቢ የራሱን ፊልሞች በጀት እንዲሸፍን ዋስትናውን ተጎናጽፎአል፡፡

    አብዛኞቹ የሆሊውድ ፊልም አዘጋጆች በቅድሚያ ያዘጋጃቸው ፊልሞች ላይ የሚጠቅሟቸው ትእይንቶች ላይ እንኳን የመወሰን መብት የላቸውም፡፡

  ጆን አቪልድሰን እንደሚናገረው ‹‹ ከሮኪ በኃላ እንዳዘጋጃችው የሚደርሱኝ የፊልም ጽሁፎች ሁል ግዜም ከስር ተነስተው መጨረሻ ላይ አሸናፊነትን ስለሚቀዳጁ ሰዎች የሚያወሩ ናቸው፡፡ የስቱዲዩ ኃላፊዎች የህ አዘጋጅ እንዲህ አይነት ፊልም ይዋታለታል ያኛው አዘገጅ ደግሞ እንዳለፈው አይነት ፊልም ቢሰራ በማለት የስባሉ፡፡ ››

  ባለፈው አመት የኦስካር ተሸላሚ የሆነው እና በሆሊውድ በገንዘብም ሆነ በዝና እጅግ የተሳካለት የፊልም አዘጋጅ ስቲቨል ስፒልበርግ እንኳን የንግዱ ትኩረት ያመጣውን ያልተጻፈ ህግ እና ተመሳሳይነት ያማርራል፡፡

   ‹‹ በድሮ ጊዜ ማለትም በሄሊውድ ወርቃማው ዘመን ለጥበብ ሐላፊነት መውሰድ ይሰራበት ነበር ፡፡ እነኛ አክሳሪ እንኳን ቢሆን ይህን ግምት ውስጥ በማስገባት ኃላፊነቱን ከመሸከም ወደኋላ የማይሉት ታላላቆቹ ሰዎች አልፈዋል፡፡ እናም እናደማስበው ሆሊውድን ሰለባ እና አሳዛኝ ሁኔታም ምክንያቱ ይኸው ነው ፡፡›› ካለ በኃላ ስፒልበርግ አስተያየቱን በመቀጠል ‹‹ የበፊቶቹ የስቱዲዩ ሀላፊዋች ጎበዝ በነሩ ፡፡ ለማንኛውም አሳሳቢ ሁኔታ ኃላፊነት ከመውሰድ አይቆጠቡም ዛሬ ግን ችግር አለ ፡፡ በከፍተኛ ቦታ ኃላፊነት ያለባቸው የዛሬዋቹ ባለስልጣን ይሆናል ወይንም አይሆንም ለማለት ችሎታው የላቸውም ፡፡ በንግዱ አለም የሚያዋጣ የሚመስላቸውን ብቻ ይመርጣሉ ፡፡ ይህ ሁኔታ ደግሞ በፊልም ስራ ላይ በጣም ይከብዳል ምክንያቱም ሁሉም ፊልሞች ከሰዎች ስሜት ጋር ስለሚያያዙ ሐላፊነት ሊወሰድባቸው ይገባል፡፡›› በማለት አስተያየቱን ያራዝማል፡፡

   እስቱዲዩዎች አንድን መንገድ ብቻ ከመከተል ወይንም ገበያን ፍለጋ ብቻ ከሚሮጡ የስነ ጥበብ ሰዎች ላላቸው ጥልቅ ፍላጎት ኃላፊነት ይመረጣል የሚል አለው ስቲቭን

 

ስቲልበርግ ‹‹ የፊልም አዘጋጁ ጆርጅ ሉቃስ በ1977 / ስታርስ ዋርስ/ን ሲሰራ በአሜሪካን እጅግ ተደናቂው ልጅ ሆኖ ነበር ይህ ፊልም ተመርቆ ከመከፈቱ በፊት ጆርጅ 15 ሚሊዩን ዶልር እንደሚያስገኝ ነበር የገመተው ፡፡ ነገር ግን ፊልሙ ያስገኘው የዶላር

መጠን 524 ሚሊዩን ደርሷል፡፡ ይህ ፊልም በጣም ጥሩ ውጤት ያገኛል ማለት በፍጹም አይቻልም ችኔ ለምሳሌ ዕቅዴን ሳወጣ ሁልግዜ ለመጥፎ ነው የምዘጋጀው እናም በስኬት እደነቃለሁ ›› ሲል ስፒልበርግ አስተያየቱን አጠቃሏል ፡፡ በሁሊውድ የስነ ጥበብ ዙሪያ ናግዱ የጦፈ መሆኑ እና ሆሊውድም የአለማችን የብዙ ፊልሞች መስሪያ መዲና እንደመሆኗ በፊልም ጥበብ እድገት ላይ ስለሚኖረው ተጽእኖ ምን ብለው ይሆን አሜሪካን ፊልም የተሰኘው መጽሔት ስለዚህ ጉዳይ የዘገበው የለም

v     Encyclopedia  No 4 P 114, 1986

v     American United States information agency ,1992

     
0 Comment(s).

There are no comments to this entry.

Post New Comment

 BraveJournal Member Non-Member
No Smilies More Smilies »
Please type the letters you see