
ተዋንያኖች
ተዋንያኖች ከፊልሙ ኢንዱስትሪ የገንዘብ ሰዎች ( ኤጄንቶች፤ የስቱዲዩ ኃላፊዋችና አቅራቢዎች ) የበለጡ ዝነኞች ቢሆኑም ጥሩ ተሰሚነት ያላቸው ጥቂቶቹ ምርጦች ናቸው ፡፡ ያም ተሰሚነት የሚቆየው ለተወሰነ ግዜ ብቻ ነው ፡፡ ለምሳሌ በርት ሬይኖልድስ ( ዳን ኦገስት በተሰኘው የቴሌቪዠን ፊልሙ፤ ናቫጆጆ፤ ዴሊቨራንስ እና ዘ ሚን ማሽን በተባሉት የሲኒማ ተዋንያኖች ሻርኪይስ ማሽን እና ረፍ ከት በሚል የተሰሩት የቪዲዩ ፊልሞች እንዲሁም ባለፈው አመት ጊዜ ውስጥ እረዘም ላለ ግዜ በትዳር አብረን ስንኖር በሚሊየኖች የሚቆጠር ሀብቴን አስጨርሶኛል በማለት ኩዊንቶች በማለት የማደጎ ልጃቸው ምክንያት ፍርድ ቤት ባቆመችው ሎኒ አርሰን ይታወቃል፡፡) በ1970ዎቹ ዓመታት እጅግ ምርጥ ከነበሩት ተዋንያኖች መሀል አንዱ ነበር፡፡ ዛሬ በሆሊውድ ውስጥ አነስተኛ ስልጣን ነው ያለው ፡፡ አሁን ያሉት ተዋንያኖችም ለማደግ ከፍተኛ ትግል ያደርጋሉ፡፡ ዶስቲን ሆፍማን ዛሬ በአንድ ፊልም ትወናው 20 ሚሊዩን ዶላር ያገኘ ይሆናል፡፡ ነገር ግን በ1967 በተሰራው ( ዘ ግራጁዌት ) በተሰኘው ፊልሙ ላይ በተወሰነው በሲኒማ አንድ እርምጃ እመርታ ላስመሰከረበት ፊልም ግን የከፈለው 17ሺ ዶላር ብቻ ነው ( ደስቲን ሆፍማን ቱትሲ ፤ክራመር ቨርሰስ ፤ክራመር ፤ ዘ ሬይን ማን በሚባሉት ፊልሞች ይታወሳል፡፡)
በገንዘብ ረገድ አስተማማኝ ባልሆነበት ባሁኑ ግዜ አላፊ የሆነውን ዝና ሲጎናጸፍ ተዋንያኖች እግረ መንገዳቸውን ገንዘብ ለማጋበስ መከጀሉን መተው ሳይከብዳቸው አይቀርም፡፡ ወጣትነቱን በድህነት ያሳለፈው ሲልቨስተር ስታሎን ‹‹ ማንም ሰው በፊት እንደነበተበት እንዳይመለስ ለሚያደርገው ዋስትና እጅ መስጠት ያለ ነው ነገር ግን በስራዬ ዙርያ ያለውን የንግድ ትኩረት እዚህ ላይ መቆም አለበት የምልበት አንድ ወቅት ይኖራል፡፡ያን ጊዜ ለንግድ ያልሆነ ሙከራ ፊልም ላይ ነው የማተኩረው ፡፡ ›› በማለት ሐሳቡን ገልጾአል፡፡
ይህ ሁኔታም አንዳንዴ ሳይታወቅ ያልፋል ፡፡ ኮንትራት ትፈራረማላችሁ ፡፡ ሳታስቡት አመታት ያልፋሉ ፡፡ ሆሊውድ ደግሞ በአንድ የፊልም አይነት ይወሰወናችኃል የሰራችሁት ፊልም ጥሩ ገቢ ያስገኘ እንደሆነ እናንተ ለዛ ዓይነት ፊልም ብቻ ነው የምትታጩት ሲልቨርስተር ስታሎን ሐሳቡን ሲያራዝም ‹‹ ሚል ገብሰንን ውሰዱ በ1987 የተሰራው ሌታል ዌፐን ፊልም ምክንያት እሱ ተቀበለውም አልተቀበለውም ድርሻው ውስን ይሆናል ፡፡ ›› በማለት የሆሊውድን የንግድ ትኩረት መነጽር ስነ ጥበብን እንደከለከለው በራሱ መንገድ ገልፆታል፡፡
ጆን ትራቮልታ በ1978 በተሰራው ትራዳይ ባይት ፊቨር የአፍቃሪ ጎረምሳ ድርሻው እንደተወሰነ ቀርቷል፡፡ የጉርምስና መልኩን እያጣ እድሜው እየገፋ ሲሔድ የሙያው ሕይወት ዘቀጠ ማለት ይቻላል ጆን ትራቮልታ ግን በዓንድ ዓይነት የባህሪ ድርሻ መወሰኑ ራሱ ስራ ከመፍታት እንደሚሻል ይናገራል፡፡ ምክንያቱም ግልጽ ናቸው
‹‹ ፊልም መስራትም ሆነ ገንዘብ ማግኘት የሚያዝናና ነገር ነው፡፡››ይላል በራሱ አንደበት ጆን ትራ ቮልታ ምንም ያህል ብዙ ገንዘብ ቢያገኝ ወጪውም ያን ያህል እየጨመረ መጣ የሙያ ህይወቱን ለማየት ደግሞ በውስጡ ያለውን የፈጠራ ቡቃያ እንዲለመልም መኮትኮት እንደሚኖርበት ተገነዘበ፡፡ ይህንንም ለማግኘት ‹‹ በኪነ ጥበብ እሱነቱ የሚደሰትበትን ›› ባቻ ለማድረግ መነሳት ሊኖርበት ነው፡፡ ( በነገራችን ላይ ጆንትራ ቮልታ ስቴይንግ አላይቭ፤ ግሬስ እና ቱ ኦፍ ኤ ካይንድ በተሰኙት ፊልሞቹ ከሁሉም በላይ ደግሞ ፋሽን ተከታይ ወጣቶች በተከለከሉነት የጸጉር አሰራር ቄንጡ እና የዳንስ ችሎታው ስሙ ገኖ ነበር፡፡)
ዶስቲን ሆፍ ማን እንደሚያስበው ደግሞ ብዙ ተዋንያኖች በፊልሙ አለም ያሉት ለገንዘብ ሲሉ አይደለም ‹‹ ለገንዘብ ስንል ቢሆን ኖሮ የጠየቅነውን እስከተከፈልን ድረስ ማንኛውንም ስራ እንቀበል ነበር ፡፡ ከሥር እየቧጠጥን ነው ሁላችንም የጀመርነው ፤ ሁላችንም ጠንክረን ሰራን ሁላችንም ከስራ አጥነት ነው የተሸጋገርነውና ሐሳባችን ጥሩ ስራ ለመስራት ነው ባዙ ገንዘብ የሚከፈለን ደግሞ ለካምፓኒው እጅግ ብዙ ገንዘብ እንዲያገኝ ስለረዳነው ነው፡፡
ድንቅ የትወና ችሎታውን በኪነ ጥበብ ምጥቀታቸው ወደላቁት ስራዎች ያዞረው ደስቲን ሆፍማን በሼክ ስፒር ‹‹ የቬኒሱ ነጋዴ ›› ድርሰት በብሮድዌይ መድረክ ላይ መቅረቡን ይመርጣል፡፡ ለገንዘብ ሲል ብቻ ስነ ጥበብን ሊቀይር አይፈልግም ሌሎች የሆሊውድ ተዋንያንም ተመሳሳይ ሀሳብ ነው ያላቸው ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ፊልሞቻቸውን ራሳቸው በማዘጋጀት የፊልሞቹን ጥራት ለመቆጣጠር ይሞክራሉ ፡፡ ነገር ግን አንዳንዶች ደግሞ ፊልም ማዘጋጀትን ከትወና የበለጠ አድካሚ ሆኖ ያገኙታል ‹‹ ፊልም ሳዘጋጅ ይላል ሲልቨስታር ስታሎን “ ህይወቴ ጥዘበራረቃል፡፡ ” አዘጋጆቹስ ስለሆሊውድ ምን የሚሉት ይኖራቸዋል ፡ እሱን በሌላ አጋጠሚ እናነባለን፡፡