Powered by Bravenet Bravenet Blog

Tag Board

This tag board is currently empty.

Please type in the four characters shown in the black box.

Tuesday, February 24th 2009

5:20 AM

ሺርሊ ማክሌይን

ሺርሊ ማክሌይን

 

‹‹ ብሪንግ ሚዝናድ ኦፍ አልፍሬድ ገርሲያ ‹‹ አዲስ አበባ በሚታይበት ወቅት ሲኒማ ቤቶች ሁሉ በነበራቸው አቅም ነበር የሚንቀሳቀሱት፡፡ በዚህ ፊልም ላይ ዋናውን ባህርይ የሆነው ተዋናይ ዋረን ቤቲ ይባላል፡፡ አተዋወኑ በትክክለኛው ሕይወቱ የሚኖር ነበር የሚያስመስለው፡፤ ለጨዋታው ያህል አነሳሁት እንጂ ላቀርብላቸው የፈለግሁት ሺርሊ ማክሌይንን ነው ፡፡

 

     ‹‹ በአደጋ ውስጥ›› በሚለው የሕይወት ታሪክ መጽሐፉ እንደጠቀሳቸው ዋረን ቤቲ ታላቅ ወንድሟ ነው፡፡ የሠማቸውን መለያየት ያመጣው እሷ ለኪነጥበብ ሙያዋ ስሟን የወሰደችው ከናቷ በመሆኑ እንደሆነም በዚሁ መጽሐፍ ገልፃለች፡፡

     በሲኒማ ዓለም ተሳታፊ ከሆነች ከ35 ዓመታት በላይ አልፈዋል፤፤ ‹‹ወንዲላዋ ልጋጃገረድ››፣ ‹‹ሩህሩህዋ ኢርማ›. ከተባሉ እጅም ጥሩ ስኬት ካስገኙላት ፊልሞች በኋላ በሠራቸውና ለዚህም ድንቅ ትወና ‹‹አስካር›› ለተሸለመችበት ‹‹ የርህራሄ ጊዜ በተሳለው ፊልም የአሜሪካንን ሲኒማ አፍቃሪዎች በእንባ እንዲታጠቡ አድርጋለች፡፡ ፊልሙ በእናትና ሴት ልጅ መካከል ስላለው ግንኙነት የሚገልጽ በአጥጋቢ ደረጃ የተዋጣለት ሆኗል፡፡

‹‹ሃሪን ማን ገደለው? ‹‹ በሚለው የአልፍሬድ ሂችኮክ ፊልም ነበር መጀመሪያ የተሳተፈችው ከዚህ በኋላ ቪንቼንቲ ሚኔሊ፣ በቶሪዮ ዲሲካ፣ ሮበርት ባይስ እና ቦብ ፎስን የመሳሰሉት የፊልም አዘጋጆች በርሷ እርዳታ ለሥራ ያላት የማይጠፋ የፍቅር ፍም በልቧ እንዲያድር፣ ስሜታዊና የትወና አድማሷ የሰፋ ተዋናይ እንድትሆን ሸርሊ ማክሌይንን በመቅረጽ በኩል ቀዳሚውን ሥፍራ ይዘዋል፡፡

     ቀደም ካሉ ዓታት ጀምሮ የተዋናዮችን የሕይወት ታሪክ በተመለከተ ከተጻፉት መጻህፍት የሸርሊ ማክሌይን ከሥር መሠረቱ የተለየ በመሆኑ በጥሩ ሁነታ በመፃፉ አንድ ሃያሲ ሆነ ጋዜጠኛ ጣዕም በማጣት የወነጀላት አልነበረም፡፡

     የፊልም ጠብቶች እንደሚናገሩት ‹‹ የርህራሄ ጊዜ›› ላይ ያለው ትወና ከአስተማማኝ ችሎታዋ የሚፈልቅ አንፀባራቂ ማስረጃ ነው ይላሉ፡፡ ስለፊልሙ ስኬትም ስትናገር ‹‹የሁላችንም ችግር በፊልሙ ውስጥ ተንፀባርቋል፡፡ እናት ምን ጊዜም ከልጇ ጋር የተወሰነ አለመግባባት ይኖራታልና፡፡ ‹‹ብላለች ተመልካቹን እሱነቱን ያስረሳው ግን የሷ ድንቅ አተዋወን እሎታ በደማቁ ሊሰመርበት ይገባል፡፡

 


0 Comment(s).

There are no comments to this entry.

Post New Comment

 BraveJournal Member Non-Member
No Smilies More Smilies »
Please type the letters you see