
ተንኳሹ ኒክ ኖልት
በአዲስ አበባ ውስጥ በአንዳንድ የቪድዮ ፊልም ማሳያ ቤቶችና የመንግስት ሲኒማ አዳራሾች 48 ሰኣታት የሚል ርዕስ ያለው ፊልም በታዋቂው ጥቁር አሜሪካዊ ኤዲ መርፌና ኒክ ኖልት ተዋናይነት ለሀገራችን የፊልም አፍቃሪዎች መቅረቡ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፡፡
ወንጀለኛን የሚከላከል ቆራጥ ፖሊስ ባሕርይ ተላብሶ የተጫወተው ኒክ ኖልት አሁን ያለበት ደረጃ ለመድረስ ቀላል ያልሆኑ የሙያ ውጣ ውረዶችን አሳልፏል፡፡ ሆሊውድና ነክ ኖልት ብዙም የተጣጣሙ አልመሰሉም፣ ባለፉት ዓመታት፡፡ ግን ለምን እንዲህ ሆነ? በዚህ ፈጣን በሆነ የፊልም ኢንዱስትሪ ኖልት የራሱን ችሎታ በመጠቀም ጥሯል ግሯል፡፡ ጥረቱ ራሱን ሊያረካው አልቻለም፡፡ ሆሊውድ ውስጥ ያለው የወሬ ብዛትም ያናድደዋል፡፡
‹‹ ውድቀት በቤሸርሊ ሂልስ›› በአሜሪካን የመጀመሪያው ትዕይንት ሲታይ ለገዜጠኛ ኢንተርቪው ሰጥቷል፡፡
ለምን ይህን ያህል ወሬ እንደሚነዛ አይገባኝም አንድ ሰው የጭነት መኪና መንዳት የሚወድ ቢሆን ሾፌር ይሆናል፡፡ እኔ ኮከብ ልሆን አልፈልግም፡፡ የፈለግሁት ተዋናይ መሆን ብቻ ነው፡፡ ‹‹ በማለት ምሬቱን ገልጿል፡፡
ሀብታም፣ ድሃ የሚለው አቻጭር የቴሌቪዢን ተከታታይ ፊልም ግን ኒክ ኖልት ያሰበውን ያህልም ባይሆን ኮከብ አድርጎታል፡፡
ለአንዳንድ ፊልሞች ኮንትራት እንዲፈረም ጥያቄ ሲቀርብለት አልፎ አልፎ ይቀርባል፡፡ ሊሰራቸው ለሚመኛቸው ፊልሞች ደግሞ የሁለተኛ ደረጃ ጋራንት ይሰጠዋል ልክ እንደ ተቀያሪ ተጫዋች ደከም ባለ የፊልም ጽሁፍና አመቺ ባላሆነ የስራ ቦታ የማይታረሙ ስህተቶችንም ታዝባል በአብዛኘው ግን ከደግ አሳቢ መካሪዎች ይልቅ ውስጣዊ ልቡን/ሕሊናውን ያዳምጣል ጥንካሬውን ላለማጣት ሲል/
ሰሜናዊው ደላስ ቁ 40 እና የተያዘው መንገድ በሚባሉት ፊልሞች አላማረረም ተቀባይነትን በበቂ ሁኔታ አግኝተውለተናልና፡፡ የተያዘው መንገድ›› ላይ ስለሚመከተው ባህርይ ሲናገር ዶክ ብቸኛ ነው፡፤ ዕድለ ቢስና ገለልተኛ፡፡ ሙሉ በሙሉ የራሱ የሆነ ሰው ያም ሆኖ ግን በጥሩ ሁኔታ የሕይወት አሳዛኝ ገጽታዎች ስለሚረዳ በሀዘን የተሞላ ለስላሳና ሩህሩህ ነው፡፤ ከሉዚ ጋር በሚፈጥረውም ወዳጅነት ብቸኝነቱ ብርሃን ይፈነጥቅበታል፡፡ እኔም ከዚህ ሰው ጋር ሙሉ በሙሉ አመሳስላለሁ፡፡ በማለት ይገልፃል፡፡
የዚህ ፊልም ሥራ ቀረጻ በአስቸጋሪ የሥራ ሁኔታዎችም ስለነበረ የአክተርነት/ የተዋናይነት/ ሙያ ኖልት እንደሚያስበው ቀላል ሆኖ አላገኘውም፡፡
በኔብራስከ ስቴት አማሃ ውስጥ በ1941 ዓ.ም ነበር ተወለደው፡፡ አባቱ ፍራንክ ኖልት ዝነኛ የአሜሪካን ፊትቦል ተጫዋች ስለነበረም ከሞትም በኋላ በኳሱ ጨዋታ ስሙ ይታወሳል ኒክም ቢሆን በኳስ ቸዋታ ብዙ ሽልማቶችን ተቀብሏል፡፡
1962 ዓ.ም ከከተማው ኮሌጅ ከለቀቀ በኋላ ለ12 ኣመታት በተለያዩ የክፍለ ሀገር የቴያትር መድረኮች ላይ ተሳትፏል፡፡
በሆቴሎች በቆርቆሮ የታሸገ ማካሮኒ በመመገብና ምሽቱንም በማሳለፍ ኖልት የትወናውን ስልት መካን ብቻ የጥበቡም ፍቅር አድሮበታል፡፡ በአንድ ወቅት ኒው ዮርክ ሄደና ትዕይንት ተካፈለ አልተዋጠለትም ነበር ከዚያ ትልቅ ከተማ ሹልክ ብሎ ጠፋ፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ከትላልቅ የቴያትር ማእከላት በመራቅ አሳለፈ፡፡ የሱሰኞች መጨረሻ ማጨሻ ክፍል የሚለው የዊሊየም ኢንጌ ድርሰት ወደ ሉስ አንጀለስ አመጣው፡፡
ኖልት ግን በምዕራቡ ዳርቻ ለመቆየት የተለየ ፍላጎት አልነበረውምና ቺካጎ ወደሚገኘው ጉደማን ቴያትር ለመመለስና ለመሞከር ፈለገ፡፡ ወዲያው ቴሌቪዢን አካባቢ ሥራ ጀመረ ወደቴያትር መድረክ ከዚያ በኋላ አልተመለሰም፡፡
ሀብታም፣ ድሃ የሚለው የቲቪ ፊልም ላይ ከሥራ በኋላ በ70 ዎቹ አጋማሽ ላይ ዝናን አተረፈ፡፡ ከዚያ 48 ሰዓታት የሚለውን የወንጀለኛ ተከታታይ ባሕርይ ተላብሶ እንደተጫወተና የዚህ ፊልም ሥራ ካለቀ ከጥቂት ቀናት በኋላ በእሳት ውስጥ በሚለው ፊልም የፎቶ ጋዜጠኛን ባህርይ ወክሎ ሰርቷል፡፡
ሀብታም ድሃ የሊለው ፊልም በቴሌቪዥን ሲቀርብ ነበር ካተሪን ሄፕበርን የምትባለው ዕውቅ የሲኒማ ተዋናይ የፊልም ድርሰት እንዲያየውና ከተስማማው ሃሳቡን እንዲገልጽላት የላከችው ድርሰት የግሬስ ኩዊግሊ የመጨረሻ ዕጣ የሚል ርዕስ ነበረው፡፡ ኖልት ድርሰቱን ተመለከተውና ስምምነቱን ገለጸ፡፡ ይህ በሆነ በ5 ዓመቱ የፊልሙ ሥራ ሲጀመር በመጀመሪያው ቀን ኖልት መድረስ ከነበረበት አንድ ሰዓት አርፍዶ አርቲስት ስሆነችም ዕድሜዋደ ወደ 78 ደርሷል በዚያን ጊዜ የሶስት አስካር ሽልማቶች ባለቤት ነች፡፡ ይህን ጊዜ በንዴት ጨሳ ኖሯል፡፡ ስለዚህ የስድቡን መዓት ታወርድበታለች ‹‹ ማይም፣ያልተገራህ፣ ከዚግ ግባ የማይሉት ጅል!!!! ጮኸችበት፡፡
‹‹ ይቅርታ ያደርጉልኝ ›› በማለት አጉረመረመ ኖልት፡፡
‹‹ ይቅርታ ለመጠየቅ አትቸገር ‹‹ ከተሪን በንዴት፡፡
‹‹ በእውነት ግን አዝናለሁ፡፡ ‹‹በማለት ኖልት ተናግሮ መልስ ሳይጠብቅ ወደ ፊልም መቀረጫው ቦታ ሄዶ እየዋኘም ርቆ መሄድ ስለመበር ሲዋኝ ሄኘበርን ድንጋይ ላይ ቆማ እያየችው ›› እንደምትሰምጥ ተስፋ አደርጋለሁ›› አለች ድምጿን ከፍ አድርጋ፡፡
በዚህ ዓይነት ድምር ብዙዎች አጨራረሱ እንደሚበላሽ አድርገው ነበር ገመቱት፡፡ ነገር ግን በከተማው ኖልትና በተናዳጇ ካትሪን ትልቅ ጓደኝነት መሰረት ነበር፡፡ ከዕድሜዋ አኳያ አስተያየት የሚሰጡም ይህ ፊልም የመጨረሻዋ እንደሚሆን ሲናገሩ ይሰማሉ፡፡
ኖልት ስላካትሪን አተዋወን ሲገልጽ ‹‹ በሚታይ ድንቅ የሆነ ችሎታና ምንም ሳትጨነቅ ነበር የምትሰራው እንዲያውም አንድ ግዜ ቀረጻ ላይ እያለን ሹፌሩን ተኩሼ እንድገለው ነገረችኝ ሁኔታው አሳቀኝ ዝም አልኩ አንድ ጥፊ አቀመሰችኝ፡፡ እንዲህ ዓይነት ነገር ግን በፊልሙ ድርሰት ውስጥ አልነበረም ቢሆንም ግን በጥሩ ሁኔታ ተዋጥቷል፡፡ የሷን ያህል ለመሥራት በጣም ብዙ መልፋትና መጣር እንደሚኖርብኝ አውቃለሁ ብሏል፡፡