
ሲዲኒ ሊዩሜት
ሲዲኒ ሊዩሜት ይባላል፡፡ በዘመናችን የምዕራቡ ዓለም ሲኒማ ላለው ዕድገት ተጨባጨ አስተዋፅኦ አድርጓል፡፡ አ.አ.አ ሰኔ 25 1924 ዓ.ም ፈላዴልፊያ ውስጥ ቢወለድም ብዙ አልቆየበትም ገና ሁለት ዓመት ልጅ እያለ ከቤተሰቡ ጋር ወደኒውዮርክ መጥቶ እስከ አሁን ድረስ ኖረበት፡፡ አባቱ ተዋናይ ስለነበረም ሕፃኑ ሊዩሜት ፈጣን ሆኖ መድረክን የ4 ዓመት ልጅ እያለ ተዋወቀው፡፡ በሱ የእድሜ ደረጃ ሙያቸውን ጀመሩ የሚባሉት ተዋንዮች በስታር ኪተንና ሊዛ ሚኔሊ ናቸው፡፡ በትልቁ የኢኮኖሚ ቀውስ በደረሰባቸው ዓመታት በሬዱዮ ቴያትሮች ይዳተፍ ነበር፤፤ በ1935 ዓ.ም የ11 ዓመት ልጅ ሆኖ ለሙያው መጀመሪያ ተብሎ የሚጠቀስለትን በሲዲኒ ኪንግስሊ የተዘጋጀውን መውጫ የሌለው መንገድ ተባለው ቴያትር በብርድዌይ ተካፈለ፡፡ በጉርምስና እድሜው ጥሩ የትወና ችሎታ ኖሮት በስሜቱ በመግፋቱ በፈቃደኝነት ጦር ሠራዊት ውስጥ ገብቶ ሲያገለግል በ1964 ዓ.ም ከሰራዊቱ ተወገደ፡፡
በዚያው ዓመት ስድኒ ሊዩሜት በሊ ስትራስበርግና ኤሊያ ካዘን የሚመራ የተዋናዮች ስሩዲዮ ገባ ነገር ግን ብዙም ሳይቆይ በ1947 ከፍተኛ ተዋናዮች ት/ቤት የተወሰኑ ሰዓታት እየተማረ የራሱን ብቸኛ መንገድ ለመፈለግ ተዋናዮችን በመሰብሰብ የቴያትር ቡድን አቋቋመ፡፡ የቴሌቪዥን ፍቅር ያደረበትም ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ነበር፡፡ በ1948 ዓ.ም የተዋናይነት ሥራውን በመተው በሬድዮና ቴሌቪዥን የአዘጋጅነት ሥራ ሙሉ ጊዜውን መጠቀሙ ተያያዘው፡፡
እስከ 1956 ዓ.ም ድረስ ብዛት ያላቸውን ሥራዎች በቴሌቪዥን ሥራዎች በቴሌቪዥን አቅርቧል፡፤ ከነኝህ ውስጥ ዕውቅናን ያገኘባቸው መላው የንጉስ ነገሥቱ ሰራዊት፣ ጠሳኮና ባንሴቲ ታሪክ፣ ይህ ባለ ንብረትነት የተረገመ ነው፡፡ የባቀላ ጩኸት እ ባርነትን በመቃወም ታላቅ ተጋድሎ ላደረገው ብራውን መታሰቢ የተሰራተው የጆን ብራውን ወረራ ይጠቀሳሉ፡፤
በ1957 ዓ.ም በቅልቁ ተዋናይ ሄንሪ ፎንዳ እርዳታ በሊዮሜት ጥራት ያለው ሥራ የሬጂናልድ ሮውዝን አስራ ሁለት የተናደዱ ሰዎች የሚለውን ድርሰት በቴሌቪዥን አቅርቦ ብዙ ያነጋገረና ችሎታውን ያሳበት ጊዜ ሆነ፡፡ ፊልሙ ደህና ገቢ ቢያሰገኝም በአሜራካን ሃያሲን ከፍተኛ ግምት ተሰጠው፡፡
ጊዜያት ባለፉም ቁጥር የሊዩሜት ሥራም እያደገ መጥቷል፡፡ ከ20 ዓመታት በኋላም ሉስ አንንጀለስ በሚገኘው የካሊፎርኒያ ዩኒቨርስቲ በሲኒማ ኣለም ስላሉት ታላቆች፣ የፊልም ቅንብር፣ የሌንሶችን አጠቃቀምና የብርሃንን የተለያዩ ገጽታዎች ዝርዝር ሁኔታ ትምህርት ቀስሟል፡፡
ለኔ ይላል ሊዩሜት ሲኒማ እንዲሁ በዓይናችን ስለተፈጥሮው ስለሰው ልጅ ልናይ የማንችለውን ጥቃቅን ሁኔታዎች በካሜራ አማካይነት የሚያሳየን ጥበብ ነው፡፡ በማለት ይገልፀዋል፡፡ ሊየሜት ፊልሞች ቢደረደሩ ጊዜውም አይበቃንም በሌላ ጊዜ ብንሞክርስ? እስከዚያው ሰላም