Powered by Bravenet Bravenet Blog

Tag Board

This tag board is currently empty.

Please type in the four characters shown in the black box.

Tuesday, February 24th 2009

5:24 AM

ሊተካ ማይችለው ሊኖ ቬንቱራ

ሊተካ ማይችለው ሊኖ ቬንቱራ

     ዘ ሚዘራብልስ ወይም መከረኞቹ በሚል ርዕስ አቶ ሣህለሥላሴ ብርሃነ ማርያም ወደ አማርኛ የመለሱትን የቪክቶር ሁጎን መጽሐፍ አንብባችሁት ይሆን? የዥን ባልዥን ባሕርይ ከአእምሮ ሚጠፋ አይመስለኝም፡፡ የኢትዮጵያ ቴሌቭዥንም በአንድ ወቅት የሳምቱ ታላቅ ፊልም በሚታይበት ጊዜ አቅርቦታል፡፡ ዥን ባልዥን የሚባለውን ባህርይ ወክሎ የተጫወተው በሰውነትም ሆነ በጥልቅ ስሜት ገዘፍ ያለው ሊኖ ቬንቱራ የሚባለው ፈረንዳዊ ተዋናይ ነው፡፡

     ሊተካ የማይችለው ሊኖ ቬንቱራ በሚል ርዕስ ካገኘሁት ጽሑፍ ስለ ቬንቱራ እንዲ ይነበባል፡፡

     በአውሮፓ ውስጥ ከአለን ዴሎንና ዥን ፓል ቤልሞንዶ በመቀጠል በጣም የሚፈለገው የሲኒማ ተዋናይ ሊኖ ቬንቱራ ነው፡፡ አብዛኛው ተመልካች ስሙን ከወንጀል ታሪኮች ውስጥ ካሉ ሕገወጥ ወንጀለኞች ወይም ሕግ አስከባሪ ትጉህ ፖሊሶች ጋር ያያይዘዋል፡፡ እነኝህን ባሕሪያ ወክሎ ከተጫወተባቸው ፊልሞች ሁለተኛው ትንፋሽ፣ ሁሉንም አደጋዎች ግምት ይጠቀሳሉ በነዚህ ፊልሞች ያሉት ባሕርያት ከእውነተኛ ወንጀለኝነት ይልቅ በሕይወት ተስፋ የቆረጡና ገለልተኛ ጀብደኝነት የተጫናቸው ናቸው፡፤ የፖሊስ መርማሪ የባሕርይ ምስያዎቹም በየሲሲሊያኖች ቤተዝምድና እና ደህና ሰንብት ፖሊስ የተባሉት ፊልሞች ይታወሳሉ፡፡ በረጋ መንፈስ የተቀረፁና የሚታዩት የባህርያት ነፀብራቅ ስለሆኑ የሚረሱ አይደሉም፡፡ እነኝህ ባህርያት ከሰው ልጅ የተፈጥሮ ችሎታ በላይ ያልተካኩ ነገር ግን ግብረ ገብንና የሰብአዊነት ክብርን እነሱ በሚረዱት መልክ ቃላታቸውን ጠብቀው ለፍትህ መገኘት ጠንካራና የዳበረ ስሜት ያላቸው ናቸው፡፡

ሊኖ ቬንቱራ የሚጫወታቸው ባህርያ እንዳይደጋገሙበትና የፈጠራ አድማሱን እንዳይገድቡበት የተቻለውን ይጥራል፡፡ ባህርያቱ የሚመሳሰሉ ሆነው ቢታዩም እያንዳንዳቸው የራሳቸው ልዩ ባሕርይ አላቸው፡፡

     እንደሚወደው ተዋናይ ሃምፍሬይ ቦጋት ቬንቱራም ሰዎች አደጋ በሚያንዣብብቸው ወቅት የሚኖራቸውን ጠንካራ መንፈሳዊ ስብዕና አጉልቶ ያወጣል፡፡ የተረጋጉ፣ የሰከኑና ለምክንያት ራሳቸውን የሚሰጡ ሰዎ አድርጎ ነው ወክሏቸው የሚጫወተው፡፡ ቬንቱራ በሲኒማ የራሱን አተዋወን ስልት ለማዳበር የግሉን መንገድ ቢከተልም ጋዜጠኖን ሁለተኛው ጋቤት የሚል ቅጥያ እንዳይለጥፉበት ሊያግቸው አልቻለም፡፡ /ጋቢን የተባለው ተዋናይ ዘ ሲሲሊያን ክላክ በሚለው ፊል ላይ የቤተሰቡ አባወራ ሆኖ የተጫወተው ነው፡፤/

     መጀመሪያው ስኬቱ የታየው በዥሊየን ዲዮኒኒዬ ማሪ ኦክቶበር በተባለው ፊልም ላይ የተቃዋሚ ወገኖች ቆራጥ ታጋይን ባሕርይ ሲተውን ሲሆን በዚህ ቁጥብና ግልፅ ጨዋታው ወጣቱ ቬንቱራ በፕሮፌሽናል ተዋናይን የሚለዩተር ነጥቦችን በትክክል በእጁ እንዳስገባቸው አስመስክሯል፡፡

     70 ርዕሶች በተካተቱበት የሊኖ የሕይወት ታሪክ መጽሐፍ ውስጥ በንግዱ የሲኒማ ዘርፍ የሚቀርቡለትን በጥንቃቄ ያልተዘጋደጁትን ሥራዎች ያለማቋረጥ እንደተቃወመ ገልጿል፡፡

     በፈረንሳይም ሆነ የጣሊያን ፊልሞ ኮከብ ሆኗል፡፡ ዛሬ ከሚቀርቡለት የባሕርያት ድርሻ ማይመስለውን አይቀበልም፡፡ ችሎታቸውን ካላስመሰከሩ የፊልም አዘጋጆችም ጋር ለሥራ አይነሳም፡፡

     ሊኖ ቬንቱራ ኢሚሊዮ ቦሪን በሚል ስም ፓርማ በምትባል የጣሊያን ከተማ ከችግረኛ ቤተሰብ በ1919 ዓ.ም ተወለደ፡፡ ቤተሰቦቹ ወደ ፓሪስ ሲሰደዱ የ8 ዓመት ልጅ ነበር፡፡ ትንሽ እያለ በጣም አስቸጋሪ ነበር፡፡ በረባሽነቱም ክት/ቤት ተበሯል፡፡ የሆቴል ቤት ተላላኪ፣ አውቶ ሜካኒክ፣ ሾፌር ሀ ተጓዥ ነጋዴ፣ እና በመጨረሻም ነጻ ትግል ጨዋታን ሞያው አድርጎለት ነበር፡፡ በዚህ ሁሉ ጊዜ ግን ፊልምን ገሸሽ አላደረገውም፡፡ በቀን የተወሰኑ ፊልሞች ይመለከት እንደነበር በአንደበቱ ተናግሯል፡፡ ጊሪ ኩፖርን፣ ስፔንሰር ትሬሲንና ጀምስ ኬግኒን ያደንቃል፡፡ በ1950 ዓ.ም የአውሮፓ ነጻ ትግል ሻምፒዮና ሆኗል፡፡

     ተፈጥሮአዊ አቀራረቡ፣ ቀጥተኛነቱና ስሜታዊነቱ በፊል ኢንስትሪ ባለሙያዎችና ባለንብረቶች ዘንድ ታዋቂነትን አትርፎለታል፡፡ በሚጫወተው ባሕርይ አዲ ይዘት በመስጠት ለጎበዝ ተዋናዮች የሚሰጡትን ቅጥያ ስያሜዎ ጥሶ ማለፍ ይፈልጋል፡፡

     በመጨረሻዎቹ ዓመታት ንጉሳውያን ቡድኖች፣ አጠራጣሪ ሞት እና ትልቁ አደጋ የሚባሉት ፊልሞች ላይ በመሳተፍ ወደ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ፊልሞች ትኩረቱን እንዳደረገ እንገምታለን

     የሙያ ትምህርት፣ የመድረክ ልምድና የቤተሰባዊ ባሕል አጦት ሌኖ ቬቱራን በትልቁ የፊልም እንዱስትሪ ባሕር የጀልባ መቅዘፊያ እዳያነሳና ራሱን በራሱ ከማስተማር አላቀቡትም፡፡

     አብረውት የሰሩ ሰዎች ቬንቱራነ ሲገልጹት ጨዋ፣ ስለራሱ ማውራት የማይወድ ሰው፣ ጠንካራ መንፈስና ግትር ባሕርይ ይሉታል፡፡   

ታዋቂው የፈረንሳይ የፊልም አዘጋጅ ዥን ፒየር ሜልቪል ሲናገር የተዋናይነትን ጥበብ አይማሩትም በተሰጥኦ ያገኙታል፡፡ ወይም ደግሞ አያገኙትም፡፡ ለምሳሌ ሊኖ ቬንቱራ ተሰጠው ድርሰት ምን እንደሚባል መቼም ቢሆን አልተማረውም፡፡ ነገር ግን ከማንኛውም ሰው በሻለ ሁኔታ ይገልፀዋል ይላል፡፡

     100 ቀኖች በፓርሌሞ ውስጥ በተባለው ፊልም ቬንቱራ የነበረው ባሕርይ ድርሻ ከማፊያ ቡድን ጋር የሞት ወይም የሽረት ትግል ያደረገው ጄኔራል ዳለ ኪያዛ እናም በ1982 ዓ.ም መስከረም ወር ላይ ፓርለሞ ሲሲሊ ውስጥ በማፊያ ቡድን ስለተገደለው ሰው ነው፡፡

ሊኖ ይህንኑ አስመልክቶ በሰጠው ኢነሰርቪ ከዚህ ጄኔራል ብቸኝነት ጋር ፊት ለፊት ስጋፈጥ ጎዘን ይወርሰኛል፡፡ የተቀነባበረ ወንጀል መቆም አለበት ብለው ለሚጮሁ ቁጥር ሌላቸው ብዙ ጣሊያኖች ንዴት ይይዘኛል፡፡ እናም በመንግስት ባለስልጣኖና በማፊ መካከል ያለው ትብብርም ንዴቴን ያባብሰዋል፡፡ በማለት ይገልፃል፡፡

የአላማችን ሕይወት የጨዋታው ሕግ እስካልተቀየረ በየአካባቢ ያለው የወንጀል ብዛት ማሰቀቁ አይቀርም፡፡ ለነገሩ የዚህ ድንቅ ከያኒ አጠር ያለው ጽሑፍ ምን ያህል አርክቷችሁ ይሆን?

ሳምንት ሌላ ይዤ ለመቅረብ እሞክራለሁ፡፡ እስከዚያውም ሰላም!!!

   

0 Comment(s).

There are no comments to this entry.

Post New Comment

 BraveJournal Member Non-Member
No Smilies More Smilies »
Please type the letters you see