
ሰማንሰዛ የሚሸን ተማሪ የነበረችና የት/ቤት አንዳንድ ልጆች መነኩሳት ለመሆን ሲመኙ እሷ ግን የጋዜጦች ሞዴል መሆን ትፈልግ ነበር፡፡ አስተማሪዎቿ ሲስተሮች ሲሰሟት ሳቅ በማለት እግዚአብሔር “ ምህረት አድርግ ” ከማለት አላለፉም፡፡ በሃሳቧ ገፍታ ሞዴል ስትሆን ሲስተሮቹ አልገረማቸውም፡፡ ከት/ቤቱ እንድትለቅ ብቻ ነበር የጠየቋት፡፡ የሳማንዛ እናት ካሮልም ትምህርቷን ምን ጊዜም መማር እንደምትችል ትናገራለች፡፡
የሳማንዘ ድንገተኛ ለዝና መብቃት ዓለምን ለዘጠኝ ዓመታት አስደንቋል፡፡ ስለሳማንዛ ሪፖርት እንዲያቀርቡ ሥራ ሚሰጣቸው ገዜጠኖችም ሌተሪ የወጣላቸውን ያህል ይደሰታሉ፡፡
ለዚህ ዝነኝነት እንዴት በቃች? የሚለው ጥያቄ ብዙዎች ያብሰለስሉታል፡፡ አንድ ወቅት ላይ ሳማንሳ 15ኛ ኣመት የልደት በዓሏን ስታከብር እናቷ ካሮል ፀጉሯን የበለጠ አሰማመረችላት አናም በፓሎራይድ ካሜራ ፎቶ ካነሳቻት በኋላ “የ83 ውብ ፊት” ለሚለው ውድድር ፎቶውን በማስገባት አስመዘገበቻት፡፡ የመግቢያው ውድድር አሸንፋ ከ19 ሌሎች ተፎካካሪዎ ጋር በመጽሔት ላይ ወጣች፡፡ ይህ የፖሎራይድ ፎቶ ነበር ለክነኝነትና ለታላቅ ዕድል ቲኬት የሆናት፡፡ ከሽልማቶቿ አንዱ ከታዋቂው የፎቶግራፍ ባለሙያ ጆንያ ከሊ ጋር የምታደርገው ምክክር ነበር፡፡
ከዚህ በኋላ ከካላንደር ማድመቂያ ልጃገርነት ወደ ፓስተር ስትሸጋገር በለንደን ጋዜጣ ገጽ 3 ሞዴደል የመሆን ዕድል አጋጠማት፡፤ በተለያዩ አቅጣጫዎችም ትችቶች ተሰነዘሩ በሄደችበት ቦታ ሁሉ እንደማንኛውም ኮከብ አርቲስት ለመቸበጥ፣ ለመዳሰስ፣ ወይም ፊርማ ለመቀበል ትቸገር ነበር፡፡
“ ወንዶች ሞዴል ሴቶችን ከቆንጆነታቸው ባሻገር ደንቆሮ አድርገው ይወስዳቸዋል፡፡ ይህም ሁኔታ ከሜሪሊን ሞንሮ ጀምሮ የነበረው ነው፡፡ ለኔ ግን ትወና ነው፡፡ ወደፊትም ፕራይቬት ቤንጃሚን የመሰለ ኩምክና ፊል ለመስራት እቅድ አለኝ፡፡ ትላለች ሳማንዛ ፎክስ
ሳማንዛ ፎክስ ሙዚቃ ዓለም ስትገባም ብዙዎች ሃያሲያን ከሷ ሙዚቃ ከባድ አተነፋፈስና የልጃገረድ ሳቅ ሌላ ለጆሮ የሚጠቅም ዜማ እንደማይጠብቁ ተናግረዋል፡፡
የመጀመሪያ ሙዚቃዋን ገና ት/ቤት እያለች “ለመሸነፍ እልም” በሚል ርዕስ በ1982 ነበር ያወጣችው፡፡ ዕውቅናደ ያገኘችበት ቢሆንም ሸክላው ድራሹ አልተገኘም፡፡ የልድህነት ጊዜም ስለነበረ ሙዚቃዋን ማከፋፈል እንደነበረባት አላወቀችም፡፡ ሱቅ ውስጥ ገብታ የሳማንዛ ፎክስን ሙዚቃ ብትሰጡኝ በማለት ስትጠይቅና እንደሌላ ሲነገራት ተስፋ ወደ መቁረጡ አዝማሚያ ደርሳ ነበር፡፡ የኋላዎቹን ዘፈኖች ስታወጣ ግን እንደዚህ ኣይነት ስህተቶች አልደገመችም፡፡ “ተች ሚ አይ ወንድት ዩር ቦዲ” ዱ ዩ ዋን ፕሊዝ ሚ” የሚሉት ተዋቶላታል ቆንጆ ክፍያም አግኝታባቸዋለች፡፡ በእንግሊዞች የሙዚቃ ቻርት ውስጥ “ተች ሚ” የሚለው ዘፈኗ ቁጥር 3 ሆኖ ቆይቷል፡፡ በአብዛኛው አውሮፓ አገሮች ውስጥ ከሚጠቀሱት 10 ዘፈኖች ውስጥ የሷም ዘፈን ይጠቀሳል፡፤ በአውስትራሊያ ደግሞ ሁለት ጊዜ በብሔራዊ ቻርቶች ቁጥር 1 ነበር፡፡
በመጀመሪያ እውቅ ሞዴል፣ ከዚያም የተዋጣላት ዘፋኝ ሆነችው ሳማንዛ ፎክስ የሚቀጥለው ግቧ ተዋናይ ለመሆን ነው፡፡ ፍላጎቷን ከጥረቷ ከደበለችው የማይሆንበት ምንም ምክንያ አይኖርም እላለሁ በበኩሌ ሃያስያን መንገዱ ሁሉ ለሳማንዛ ቀና ሆኖላታል፡፡ ሌሎች ሕጋዊ ያልሆኑ ዘዴዎች የሚጠቀም ሰው ነው በቀላሉ የሚቀናው ይላሉ ያላዩት ነገር ግን የሳማንዛን ሌሎች ተሰጥኦዎች ነው፡፡
ሁሉም ነገር ግን ቀላል አልነበረም፡፡ አንዳንድ ጊዜ ሳማንዛ ፎክስም የረሷ አስቸጋሪ አጋጣሚዎችም አሏት፡፡ ለምሳሌ አንድ ወቅት ላይ ለቪኖ ቤት ፈቃድ ለማግኘት ባለሥልጣት መሥሪያ ቤት ሄዳ ከ15 ደቂቃ በላይ ከቪኖ ንግድ ጋር የሚሰራባቸው የተፈቀዱት ሰዓት ጋር የተያያዙ ጥያቄዎ መመለስ ተቸግራ ነበር፡፡ ደጉ ባለስልጣን ግን ራርቶላት ፈቃዷን በእጇ አግብታለች፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ሁኔታ ግን የመኪና መንጃ ፈቃድ ፈተና ላይ አልገጠማትም፡፡ ለፈተና ሶስት ጊዜ ቀርባ ሶስት ጊዜም ወድቃለች፡፡ መኪና ውስጥ ስትቀመጥም መሪው ጋር አትደርስም ሚለው አሉባልታም የተጋነነ ነው ብሎታል ቫራይቲ ሚለው የሷን አጭር ታሪክ የዘገበው መጽሔት፡፡ በሱ ደግሞ በሌላ ጊዜ ሌላ ይዤ አቀርባለሁ፡፡ እስከዚያው ሰላም፡፡