Powered by Bravenet Bravenet Blog

Tag Board

This tag board is currently empty.

Please type in the four characters shown in the black box.

Tuesday, March 3rd 2009

4:10 AM

በፊልም: ህይወት

ማውጫ

  1. በድርሰት በፊልም አዘጋጅነትና በተዋናይነት እስካር ተሸላሚዎች

ሀ. ቻርሊ ቻፕሊን

ለ. ኦርሰን ዌልስ

ሐ. ሲልሽስተር ስታሎን /ታምቦ/

  1. የቱት አባት ፊልም ተሳታፊዎች

ሀ. ፍራንሲስ ፎርድኮፓላ

ለ. ማርሎን ብራንዶ

ሐ. አል ፓኪኖ

መ. ሮበርት ዶ ኒኖ

  1. በፊልም ተዋናይነት የማይረሱ

ሀ. ጃፍ ቻንድለር

ለ. ጌሪ ኩፐር

ሐ. ቻርለስ ኮበርን

  1. ጣልያናዊ ተዋናዮች

ሀ. ጁሊያኖ ጄማ

ለ. ፍራንኮ ኔሮ

ሐ. ሊ ማሳሪ

  1. የሆሊውድ ሴት ተዋንያን

ሀ. ጁሊ አንዲሪውስ

ለ. ጆአን ኮሊንስ

ሐ. ሜሪል ስትሪፕ

  1. የሙያ ልዩ ተስጥኦ ያላቸው

ሀ. ስታቨን ስፒልበርግ

ለ. ቻርድ ቻምበርሊዶን

ሐ. ፒቶር ኦ ቱል

  1. ከሴት ተዋንን ህይወት በጥቂቱ

ሀ. ኤልሳቤጥ ቴይለር

ለ. ጄኒፈር ቢልስ

ሐ. ሜሌኔ ግሪፊትዝ

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

ቻርሊን ቻፕሊን

ቻርሊን ቻፕሊን ሚያዚያ 16. 1989 በለንደን ከተማ ቻርለስ ስፒንሰር ቻፕሊን የሚለውን ስም መጠሪያው በማድረግ ተወለደ፡፡ ዝናን በማትረፉም በስሙ ላይ ስር የሚለውን ቅጥያ ለማግኝት በቅቷል፡፡ በአሜሪካን ድምጽ አልባ ፊልም ላይ የአሳዛኙ ዘዋሪ ልጅን በመፍጠሩ በዓለም ደረጃ ዝናን ያተረፈ ትውልድ እንግሊዛዊ፣ አሜሪካዊ ዜግነት ያለውን ተዋናይና የፊልም አዘጋጅ ነው፡፡ ወደ ሲኒማው ዓለም በ1917 ከገባ ከሁለት ዓመት በኋላ በሀገሪቱ ውስጥ ካሉት የተከበሩ ሰዎ አንዱ ሆኗል፡፡ በ1920 መጀመሪያዎች ገደማም ችሎውን ለመጠቀም የትኛውም ስቱዲ ስላልደፈረ (የሚከፈለው ገንዘብ በጣም ብዙ ነበርና) ራሱ በሚያቀርባቸው ፊልሞች ብቻ መተወን ጀመረ፡፡ በ1920ዎቹ መጨረሻ ዓመታት ላይ ድምጽና ፊልሞችን በማቀናጀት መስራት ሲጀምር ጥቂት ፊልሞች ቢሰራም እነዚህ ሥራዎቹ ብዙ ሳይቆዩ ዝናውን ቀነሱበት፡፡ ቀደምት ሥራዎቹ ግን በፊልም ስራ ጥንታዊነታቸው አዳዲስ አድናቂዎች አፈሩለት፡፡ ከቻፕሊን ድቅ አስቂ ሥራዎች /1921/ /ትንሹ ልጅ/፣ /1931/ የከተማ መብራቶች /1936/ የሰለጠኑ ጊዜያት እና /1940/ አምባ ገነት የሚሉት ፊልሞ ይጠቀሳሉ፡፡ ከዳግማዊ ንግስት ኤልሳቤጥም በ1975 ስር የሚለውን ማዕረግ ተቀበሏል፡፡

 

የሙዚቃ አዳራሽ ዳንኪረተኞች ከነበሩት ቻርለስ እና ሃና ቻፕሊን ከተማቡት ወላጆች የተገኝው ቻርሊም 8ቱ የላንክቫየር ወጣቶች በሚባለው ቡድን ውስጥ በ8 ዓመቱ ነበር የኪነጥበብ መድረክን የረገጠው፡፡ ይህ የሆነውን አባቱ በሞተና እናቱ አሁንም የአእምሮ በሽተኞች ሆስፒታልን መጎብኝት ከጀመረች በኋላ ነበር፡፡ የቻር ሕይወት የአዳሪ ት/ቤቶች፣ የሕጻናት ማሳደጊያ ቦታዎችና አልፎ አልፎ መንገድ ላይ በሚኖርበት ጊዜ የመድረክ ትዕይንቶች ጋር የተያያዘ ነበር፡፡

 

የ17 ዓመት ዕድሜ እያለ በግማሽ ወገን ወንድሙ በዚያን ጊዜ የእንግሊዝ ቫውዲሺልድርጅት በፍሬድ ካርኖ ካምፓኒ ውስጥ ይሠራ ነበርና ቦ አገኝለት፡፡

 

እስከ 1913 ዓ.ም ድረስ አጫጭር የኩምክና ተዕይንቶች በማቅረብ ከካርኖ ጋር ቆይቷል፡፡ ማክ ሌኒት የኪስቶኖች ስላፕ ስቲክ አቅራቢ በኒውየርክ ከተማ ውስጥ ቻፕሊን ከካርኖ ጋር ሲሰራ ያቀረበውን ትዕይነት ተመለከተና የኪስቶን ካምፓኒ ለሚያዘጋጃቸው ፊልሞች ውል ተዋዋለ፡፡ ይህ የሆነው ከሚያዚያ ወር 1913 ዓ.ም ጀምሮ በሳምነት 150 ዶላር እየተከፈለው ለመስራት ነው፡፡ ከዚህ ጊዜ በኋላ ወደ መድረክ አልተመለሰም፡፡

 

ቻፕሊንም ዝነኛ አለባበሱ ላይ ደረሰ፡፡ የፈረሰ እሽቅድድም ባርኔጣ፣ ጠበብያለ የሴት ኮት፣ ባጊ ሱሪና ወደ ፊት ቮል ያለ ጫማ ሪዝ እና ከዘራ በሳምንት ሁለት ፊልሞች እየሰራ ቢያወጣም ገና ከጅምሩ በግሩም ሁኔታ የተዋጣላቸው ነበሩ፡፡ ብዙም ሳይቆይ የራሱን ፊልም እንዲያዘጋጅ ተፈቀደለት፡፡ ደሞዙም በሳምነት ወደ 1.250 ዶላር አደገ፡፡  

 

ከሁለት ዓመታት በኋላም በጊዜያችን ትል ከሆኑት ሁለት ሌሎች ተዋንያን ሜሪ ፔክፎርድ እና ዳግላስ ፊየርባንክስ እና የፊልም አዘጋጁ ዲ ደብሊው ግሪፊትዝ ጋር በመሆን የናይትድ አርቲስትስ የተባለውን የፊልም ድርጅት ሲመሰርቱ የየራሳቸውን ፊል እያቀረቡ ማሰራጨት እንዲያስችላቸው ነበር፡፡ /1923/ /የሃይማኖት ጉዞ/ ሰርቶ የመጀመሪያው ብሔራዊ ውል ሲጠናቀቅ በ1966 /የሆንግ ኮንግ አንደራሴ/ የሚለውን ለዩ ኒቨርሳል ድርጅት እስከሰራ ድረስ ለራሱ የፊልም ድርጅት ብቻ ነበር የሚያቀርበው፡፡

 

የቻፐሊን በዝና ደረጃ ወደ ላይ መመንጠቅ ከፊልም ታሪክ ሴራና ርዕስ ይልቅ የፊልም አሻሻጥ ስራው በመሪው ተዋናይ ታዋቂነት አየሆነ መምጣቱ የማይናቅ አስተዋጽኦ አድርጎለታል፡፡

 

የቻፕሊን የስክሪን ስብዕናው በሕዝቡ ዘንድ ተናፋቂ ተቀባይነት ከፔክ ፎርድ ፊየርባንክስና የሌሎችም ጋር ተዳምሮ መዋቅሩን ሊያጣናክረው ችሏል፡፡

 

የቻፕሊን የግል ሕይወት ማዕበል እንደበዛበት ባሕር ዓይነት ነበር፡፡ 4 ጊዜ አግብቷል፡፡ ሜልድሪድ ሐሪሰን /1918/ ሊታ ግሬይን /1924/ እና ፓውሌት ጎዳርድን /1936/ እና በ1943 የጸሐፊ ተውኔት ኤውጌኒ ኦ ኒልን ሴት ልጅ እና ኦ ኒልን አግብቷል፡፡

 

የመጀመሪያዎቹ ሁለት ፍቼዎች የጋዜጦችን የመጀመሪ ገጾች አጣበው ነበር፡፡ በ1944 ዓ.ም ፍርድ ቤት የአባትነት መብቱን ለማሳወቅ በተደረገበት ክስም እንዳዘው ነበር፡፡ በ1942 ዓ.ም ቻፕሊን ጀርመንን ለመውጋት በታቀደው ጦርነት በነበረው ፖለቲካዊ አቋም አሜሪካዊ ለመሆን እንዳልቻለ በመጠኑ ነቀፊታ ደርሶት ነበር፡፡

 

በ1947 የስራው /አቶ ቬርዶክስ/ በተሰኝው ፊልም የአሜሪካንና ሌሎችንም ፊልም ድርጅቶች አስቀጥቷል፡፡ ባለፉ ቀረጦች ከፖለቲካ ሰዎችና አንዳንደ የአምድ አዘጋጆች ጋር በማያያዝ የአሜሪካ መንግስት ተጽዕኖ ስላደረገበት በ1952 አሜሪካንን ለቆ ሄዷል፡፡ ወደ አሜሬካን ተመልሶ የመግባት መብቱ በአሜሪካን የፍትህ መምሪያ በኩል እንደሚያስጠይቀው ተነግሮት በ1953 እንደገና የመግቢያ ቪዛውን ጄኔቫ ውስጥ አግኝቷል፡፡ ቻፕሊንገና ቤተሰቦቹም ከዚህ በኋላ በኮርሲየር ሱር ሼሼይ ስዊዘርላንድ ውስጥ ኖሯል፡፡

 

በ1957 /በኒውየርክ ውስጥ ያለ ንጉስ/ በለን ደን ውስጥ አቅርቦታል፡፡ ይህ ፊልም የኮሚኒስቶ ሃሳብ እንዳለው ተደርጎ በመወሰዱ አዲስ ነቀፋ ቢስነዘርበትም ቻፕሊን አልተቀበለው፡፡ በ1966 የሆንግ ኮንጓ እንደራሴ የተሰኝውን በመጻፍ በመዘጋጀትና ለቅጽበት በቀወነበትና ፊልም ዋነኞቹ ተዋናዮች ማርሎን ብራንዶና ሶፊያ ሎሬንስ ተጫወተዋል፡፡ በ1972 ከፊልስ ሰነ ጥበብና ሳይንስ ልዬ ሽልማት ለመቀበል ወደ አሜሪካን ተመልሷል፡፡ ታህሳስ 25 1977 ዓ.ም ከሴዮር ሼሼይ ስዌዘርላንድ ውስጥ አርፏል፡፡ ነፍስ ይማር፡፡

 

 

 

 

 

 

 

 

 

አርሰን ዌልስ

አርሰን ዌልስ እ.ኤ.አ ሚያዝያ 6/1915 በኬኖቫ፣ ዊስኮንሲን በምትባለው ከተማ በአሜሪካን ሀገር ውስጥ ተወለደ፡፡ የፊልም ጽሁፍ፣ ፀሐፊ፣ አቅራቢ፣ አዘጋጅና ተዋናይ የሆነው ባለሙያ ፈጠራዊ ትረካ ዘዴዎቹና የፎቶግራፍ አጠቃቀሞ፣ ቴያትራዊ ብርሃን አፈነጣጠቁና ከዚህ ጋር የሚያያዙ ሙዚቃዎች፣ ኬን የተባለው ዜጋ የሚለውን ፊልም በ1941 ዓ.ም ሲሰራ ያቀናጃቸው ነገሮ ነበሩ፡፡ ይህንን ፊልም ጽፎ አቅርቦ ካዘጋጀ በኋላ ራሱ በተዋናይነት ተጫውቶታል፡፡ ድንቆቹ አምበርሰኖች በ1942 የተሰራውንም የጻፈው ያዘጋጀውና ያቀረበው እራሱ ሲሆን እነዚህ ሁለት ፊልሞ በሲኒማው ዓለም ባለው የስነ ጥበብ ዘርፍ እጅግ ልዩ ግምት የሚሰጣቸው ነበሩ፡፡

 

ፒያኖ ተጫዋች ከነበረቸው እናቁ አርሰን ዌልስ ፒያኖና ቫዮሊን መጫወት አጠና፡፡ የ6 ዓመት ልጅ እያለ ወላጆች ተለያዩ፡፡ በ8 ዓመት ዕድሜው ደግሞ እናቱ አረፈች፡፡ በ13 ዓመት ዕድሜው በሞት በተለየው ዝነኛ የፈጠራ ሰውና የፈብሪካ ባለቤት በኩል ተዋናዮችና የስፖርት ሰዎ ጋር ተገናኝ፡፡ በ11 ዓመት ዕድሜው ዓለምን እየተዘዋወረ ጎብኝቷል፡፡ ኢሊዬኒስ ውድስቶክ በሚገኝው የቶድ ት/ቤት በሚባለው የወንዶች ልጆች የሚማሩት ገብቶ በግድየለሽነት ቢክታተልም ስለቲያትር በዛያለ ዕውቀትን ቀስሟል፡፡ አየርላንድ ሄዶ በአህያ የሚጎት ጋሪ ጉዞ በሚል የቀለም ቅብ ከመስራትና ቃለ ዘጋቢ ከመሆኑ በፊት በቼካጎ ውስጥ በሚገኝው የስነ ጥበብ ኢንስቲት የት ጥልቅ የሆነ ጥናት አካሄዷል፡፡

 

የትውና መጀመሪያ ሥራውም በ1931 ዓ.ም የበልግ ወራት ዲብሊን ውስጥ በሚገኝው፡፡ ጌት ቲያትር ቤት ሐምሌትን ሆኖ ነበር የተጫወተው፡፡ ዌልስ በጌትና አቤይ ተዋናዮች ጋር የትወና ሥራውን አያካሄደ አየርላንድ ውስጥ ቆይቷል ወደ አሜሪካን ከተመለሰም በኋላ ከካትሪን ኮርኔል ካምፓኒ ጋር ከ1933-34 ዓ.ም ድረስ በሮሜዎና ዡልየት እንደ ሜርኩቺዮ፣ በካንዲዳ ውስጥ እንደ ማርች ባንክስ እና እንደ ኦክታሺያስ ባሬት በዊምፓል ጎዳዎ ላይ የሚገኙት የባሬት ቤተሰቦች ቴያትሮ ውስጥ በመጫወት ትዟዙሯል፡፡

 

በ1934 ዓ.ም ውስጥ በውድ ስቶክ የቴያትር ፌስቲቫል በማዘጋጀት እንደ ሐምሌት ሆኖ ሲሰራ በኒውዮርክ የመጀመሪያ ሥራው ደግሞ በዛው ዓ.ም ታህሳስ ወር ላይ ሮሜዎና ዡልየት ሆኖ ነበር፡፡ በ1936 ዓ.ም በፌዴራል ቴያትር ፕሮጀክት አንዱ ክፍል በሆነው በኔግሮ ሕዚቦች ቴያትር ማክቤዝ ቴያትርን ሙሉ በሙሉ በቁጥር አሜሪካውያን ተዋንያኖች ያዘጋጀው አርስን ዌልስ ነው፡፡

 

በ1937 ሜርኩሪ ቴያትርን መሠረት ይህም ቴያትር ቤት የሼክስፒሩን ጁሊያስ ቄሳር የታወቀውን ዘመናዊ አለባበስ ስልት ያቀረበ ነው፡፡

 

የራድዬ ፕሮግራም ሥራውን በ1934 ዓ.ም መጀመሪያ ላይ የገጣሚ አርቺባልድ ማክሊይቨን የግጥም ተውኔት አዛምዶ በማቅረብ ጀመረ፡፡ በ1934-35 ዓ.ም የጊዜ ጉዞ የሚሉትን ተከታታይ ዜናዎችና በተከታታይ በቀረበው ጥላው በሚበለው የወንጀል ሚጥር ሥር የለምንት ክራንስተን ባሕርይ ለብሶ አቅርቧል፡፡ በ1938 የሜርኩሪ ተዋናዮች ከተለያዩ ዝነኛ ጽሑፎች የተዛመዱ ድርሰቶን በተከታታይ ማቅረብ ቀጠሎ፡፡ የዓለማት ጦርነት በሚለው የዌልስ ፕሮራም በመገናኛ ብዙሃን መለፈፍ ያለበት ጽሁፍ በግል ባጭ ለማስመሰል የተቀዳውን ከማርስ ፕላኔት ላይ ወራሪዎች በኒው ጄርሲ ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን የሜርኩሪ ተዋናዮች ሲያቀርቡት በብዙ ሺህ የሚቆጠር ህዝብ ማሰመሰያ ግልባጭ እንጂ እውነት እንደልሆነ ሳይረጉት ቀርተው በፍርሃት ተርበድብደው ነበር፡፡ በዚህ ሁኔታም በብሔራዊ ደረጃ ጥላቻንም አትርፈዋል፡፡

 

በ1947 ዓ.ም ከሻንጋይ የመጣችዋ ሴት እና ማክቤዝ የሚሉትን ፊልሞች አዘጋጅቶ በተዋናይነት ሰርቶበቸዋል፡፡ ብዙ ዓመታት አውሮፓ ውስጥ ከዚህ በኋላ ኖሯል፡፡ ኦቴሎን በ1952፣ ሚ/ር አርካዲንን በ1955 ዓ.ም በማዘጋጀት በተዋናይነት የተሣተፈውና ያቀረበው እዛው አውሮፓ ውስጥ ነበር፡፡ በ1958 ሆሊውድ ተመልሶ ሰይጣን የዳሰሰው የሚለውን ፊልም የተጫወተውና ያዘጋጀው እራሱ ነው፡፡ የል ፕሮቼን በ1962 ዓ.ም ዘትሪያል /ፍርዱ/ እና ካምፓናዳስ አሜዲያኖቼ /የሊሊት ደውሎች/ በሚለው በ1966 አሁንም አውሮፓ ውስጥ ነበር ያዘጋጃቸው፡፡ በ1975 ለማስመሰያ የሚለውን አዲስ ስራ ጽፎ፣ አዘጋጅቶ ተውኖበታል፡፡ በ1982 ዓ.ም ደግሞ ቢራቢሮ የተኝውን ፊልም አዘጋጅቷል፡፡

 

አርስን ዌልስ እንደ ተዋናይ ሆኖም በብዙ ፊልሞች ላይ ተካፍሏል፡፡ ከነዚህም ውስጥ፣ ጄን ኤየር /1944/፣ /ሶስተኛው ሰው/ /1949/ /1958/ /በጣም ረዥ     ሙ በጋ/ /1959/ /በ1966/ /ለሁሉም ወራት የሚሆን ሰው/ /1970/ /22 ቁጥር ያዘ/ እና /1978/ /የተጠላለፈ ጎራዴዎ/ ይገኙበታል፡፡

 

በኋላ ላይ ከስራቸው የመድረክ ስራዎም ኦቴሎ /ለንደን 1951/ እና ንጉስ ሌር /ኒው ዮርክ ከተማ 1956/ ጥየቀሳሉ፡፡

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

ሲልቨስተር ስታሎን

በ1985 በአሜሪካን አገር ባሉ የሲኒማ ቤቶች በሼትናም ውስጥ የተደረገውን ጦርነት አሜሪካኖች እንደገና ተዋገተውበት አሸንፈዋል፡፡ ለዚህ ዓለማም የተመረጠው ተዋናይ ደራሲው ሲልቨርተር ስታሎን ነበር፡፡ ጆን ራምቦ በሚል ስያሜ የቬትናም ጦረኛ በመሆን የመጀመሪያው ደም ክፍል ሁለት ውስጥ በመቶ የሚቆጠሩ የጠላት ወታደሮችን እየተኮሰ ግዳይ በመጣል ከቬትናም እስር ቤቶች ውስጥ የአሜሪካንን ወታደሮች ነጻ ሲያወጣ ያሳያል፡፡

 

የቬየትናም ጦርነትን ተመልካቹ እንደገና እንዲያስበው የሚደርገው ይህ ፊልም መሰሎች ፊልሞች ካስገኙት በበለጠ በመጀመሪያዎቹ ሁለት ሳምንታት ብቻ የበዛ ብር አስገብቷል፡፡ ራምቦን ከ1920ዎቹና 1930ዎቹ የናዚ ሲኒማ የሚወዳድሩት ነቃፊዎች፣ ትችት ሰንዛሪዎች ቢኖሩም የተሳካ ውጤት ላይ ደርሷል፡፡ ስታሎንንም ይህ ትችት አልረበሸውም፡፡ እ ፖለቲከኛ አይደለሁም፡፡ ለአሜሪካን ተሸናፊዜጎች ነው የቆምኩት፡፡ ይላል አስተያየቱን ሲሰጥ፡፡

 

ስታሎን በ1975 የባንክ ደብተሩ ላይ 106 ዶላር ሲነበብ፣ ያረገዘች ሚስቱና የተራበ ውሻው በቤት ውስጥ እያሉ የቤት ኪራዩ ያልተከፈለው ቤት አከራይ ዙሪያውን ሲያንዝብብበት ከአሜሪካን ተራ ዜጎች መሐል አንዱ ነበር፡፡ በዚህ ጊዜ ነው ሮኪን ለመጻፍ ብዕሩን ከወረቀት ያዋሃደው፡፡ የመጀመሪያውን ጽሑፍ በሶስት ቀን ተኩል ጽፎ ካበቃ በኋላ የፊልም ጽሑፍ አዘጋጅቶ እንደ ቻርሊ ቻፕሊንና ኦርሰን ዌልስ በፊልም ጽሑፍና ጥራት በድንቅ ተዋናይነት ለኦስር ተሸላሚነት መታጨት በቃ፡፡ ሮኪ የሆሊውድ የበታች ሰራተኞች ባህርይ ቢላበስም፣ ለስላሳ ልቡና ድህነት የተጫነው ቦክሰኛ ነገር ግን ሳይጠበቅ በከፍተኛ ደረጃ ለመቧቀስ ዕድል የገጠመው ባህርይ አድርጎ ስለጻፈው ለዚህ ባህርይ እንዲህ ዓይነት ኃይልና ትኩስነተት ስለ ተጎናጸፈው ሲልቨስተር ስታሎን በሃያሲን ተሞግሷል፡፡ በኋላም ላይ ከሮኪ ክፍል ሁለት /1979/፣ ሮኪ ክፍል ሶስት /1982/ እና ሮኪ ክፍል አራት /1985/ የፊልም አዘጋጅነትን ድርሻ አራ ተወጥቶታል፡፡

 

በ1982 ለመጀመሪያ ደም የጆንራምቦን ባህርይ ይዞ ሲጣወት የፊልሙም ረዳት ፀሐፊም ነበር፡፡ የፊልሙ ትኩረትም በአንድ ያልተደነቀ የጦር ጀግና በአሬጎን ከተማ ዝቃጭ ሕይወት ላይ ሲሆን ስታሎን ራምቦን ሆኖ የተጫወተው ተልጎምጓሚ፣ በማርሎ ብራንዶና በአርኖልድ ስቸዋዜንገር መካከል የሚገኝ ጡንትኛ ሆኖ ነው፡፡

 

እ.ኤ.አ ሐምሌ 6 1964 በኒው ዮርክ ከተማ የተወለደው ስታሎን ታማሚ ልጅ ነበር፡፡ ነገር ገን ወደ ጎርምስና ሲጠጋም የክብደት ማንሳት ስፖርትን ያዘውትር ነበር፡፡ በሚያሚ ዬኒቨርስቲ ውስጥ ድራማ ሲያጠና ለጊዜው የወደፊት ዕድሉ አልታየውም፡፡ በ1985 መጨረሻ ቀዝቃዛ ጦርነት በእቡጃዲ ግርግር ላይ መዋጋቱን ብዙሃኑንም አሜሪካውያን ከተሰደደው የሶቭየት ቦክሰኛ በሮኪ ክፍል አራት ላይ እንደሚያድን ማንስ ከቶ ያስበዋል?

 

የሮኪ መንገድ

ለትንሽ ጊዜ የመጨረሻው መጋረጃ ተቋርቦ ነበር፡፡ ሲልቨስተር ስታሎን ረኪ ባልቦአን ለመግደልና ለማስወገድ ያስበበት ጊዜ ነው፡፡ እንደሚታወቀው ሮኪ የራሱን ባህርይ ሊነጥቀው ትንሽ ነው የቀረው፡፡

 

ማለቴ አለ በቅርቡ ስታሎን አዋቂዎች የተማሩ ሰዎች እኔን ልክ እንደሮኪ አድርገው ይመለከተኛል፡፡ በአሜሪካን ምክር ቤት ጎብኝት ላይ አያለሁ ኤድየርድ ኬኔዲ አይተኝ የተናገረው ቃል ታዲያስ ሮኪ የምል ነው፡፡

 

ሮኪ 5 የፊልም ቀረጻው ጊዜ እንደደረሰ ስታሎን ይህን በዱላ የሰከረ ባህርይ ሊገድል ወጥቷል፡፡

 

ከሌሎች በሙሉ ይኽኛው ፊልም የኀዘን ድባብ ያጠላበት ነው ሮኪ ጊዜው አልፎበታል እንዲሞት ክፍልጋው፡፡ የፊልም አቅራቢዎች ግን አልፈለጉም፡፡ ብሏል ስታሎን፡፡ እናም ተሳክቶላቸዋል፡፡ ሽማግሌው ሮኪ ሪንግ ላይ ተወግሮና ደህይቶም እንደገና ለመቧቀስ ሌላ የፀሐይ ብርሃንን ይኖራል፡፡

 

ሮኪ 5 እንደሌሎች አይደለም ብሎ ስታሎን የተናገረው እውነቱን አልነበረም፡፡ ሮኪ 5 ላይ ያለው ቧክሰኛ ያው የቀድሞው ነው፡፡

 

ስታሎን በጓደኞች ወደ ትክክለኛ ውሳኔ በደመ ነፍስ የሚጓዝ የንግድ ሰው ነው የሚባለው፡፡ በዚህም ፊልም ሮኪን በፊት ወደ ነበረበት ደቡብ ፍላይልፊያ መንግዶች ይወስደዋል ምናልባትም የተጋደመ ስጋ በቦክስ እየመታ ይለማመድ ወደ ነበረበት ኮካንዳ ቤት፡፡ እንደሁል ጊዜውም ስታሎን የፊልም ጽሁፏን ጽፎታል፡፡ ዝርዝር ሁኔታውን ግን ከልቡ ይጫወታዋል፡፡

 

ሰማህ ወይ አለ ስታሎን ስለሉካንደ ቤቱ የፊልሙ ቅንጫቢ ምን እንደሚመስል፡፡ ሲጠይቅ ያንንማ ሰባት ብርሃን ከስክሰህ የምታየው ይሆናል፡፡ በማለት መልሷል፡፡ /በዚህ አጋጣሚም የፊልም መግቢያ ዋጋ በአሜሪካ ያወቅን አይመስላችሁም?/

 

ታሊያ ቫየርን የሮኪን ወድ ፍቅር አድሪያናን ሆኖ እንድትጫወት እንደገና አምጥቷታል፡፡ በርት ያንግንም እንደሚስት ወንድም ፖሉን ሆኖ እንዲሰራ ነገር ግን ሮኪን በማዘጋጀት ኦካር የተሸለመደውንና ሮኪ ፊልሙንም በጥሩ ፊልምነት ለኦስካር እንዲበቃ የረዳው የፊልም አዘጋጅ ጆን አቪልድሰንን ማምጣቱ ከሁሉም በላይ አያጠያይቅም፡፡ ሮኪ 5 ሮኪ መጥቶ ሁኔታ ውስጥ ተዘፍቆ ይጀምራል፡፡ የሻምፒዮንነት ዝናተነጥቋል፡፡ ገንዘቡም እድሜ ለነዚያ አጭበርባሪ የሂሳብ ሠራተኞች ምንም አልተረፈውም፡፡ ወደደቡብ ፊላዴልፊያም ከመሠረቱ ወደ ነበረበት ሄዶ ቁስሉን ያጠጋል /ያክማል/፡፡

 

ከእንዲሪያን መላ በመነሳትም ሮኪ ካለበት የሸንፈት ገዳም መወጣጫ ያገኛል፡፡ ጥሩ አስተሳሰብ ያለውና ከዚህ በፊት የሚያውቀውን ሰው የሚያስታወስበት ግጣት ቢክ ሰኞ ጋር ይገናኛል፡፡

 

ይህ ወጣት ቦክሰኛ የሮኪ ሆኖ የሚሰራውን ባህርይ ሆኖ የሚጣወተው የጆን ዋይን የልጅ ልጆች ጋር ዝምድና ያለው ቶሚ ማሪሰን ነው፡፡ በእርግ የሮኪ ፊልም ስለሆነ ብዙ የሪንግ ላይ እንቅስቃሴዎ ይታያሉ፡፡ ከጆፕ ዌይንም ጋር ባለው ዝምድናም ወጣቱ ማሪሰን ለቡቅሻው በፍላጎ ነው የሚሄደው፡፡

 

ሆሊውድ ውስጥ እንዳሉ ሰዎች በሉስ አንጀለስ ፍርድ ቤት ሞሪሰንን እንደ ሞቱት ከሆነ የአንድኛውን መንጋጋ በመስበር የሌላውን ዓይን በመጨናበስ ነበር፡፡ በትክክልም ከልብ በላይ የሆነ የመቧቀስ ፍላጎት አለው ያሰኛል፡፡

 

ሮኪ ጁኒየርን ሀኖ የሚጫወተው የ15 ዓመት ዕድሜ ያለው የስታሎን ልጅ ልጅ ሲሆን ከአባቱ ጋር ያለው ዝምድናም አደጋ ላይ እየሆነ እንደመጣም ተሰምቶታል፡፡

 

ስታሎን ሮኪን ወደነበረበት መመለሱን ደግፈውለታል የውስጥ አዋቂዎች፣ ይህ ነው ጆን አቪልድሰንንም የመለሰው ሁኔታ፡፡

 

የኦሪጅናል ጽሑፍ አባሮት ነበር፡፡ በጣም ጥሩ ነበር ገንዘቡን ሁሉ አጥቷል፡፡ መቧቀስ የማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ እናም ይሞታል፡፡ ለታሪኩ አስቀያሚ መዝጊያ ነበር የሆነው፡፡ ይላል ጆን አቪልድሰን ስለመጀመሪያው ጽሁ ሲናገር፡፡

 

እነኝህ ሰዎች ግን ምንድን ነው የሚያስቡ? ምናልባት እናወራ ስለነበረው ሮኪ ባልቦአ እንደሚውቅ ትገምታለቻችሁ?

 

አዎን የ ፈጠሩትስ እነሱ አይደሉ

 

 

 

 

 

 

 

ፍራንሲ ፎርድ ከፖሌ

ከሁሉም ይልቅ ትልቅ የሆነው ማፊያ እንደገና ለእይታ በቅቷል፡፡ የፍራን ሲስ ፎርድ ኮፖላ ያዘጋጀው የጡት አባት ክፍል 3 በሆነው ፊልም ዋና ባህርይ ዶል ሜካኤል ኮርሌዎኔ ነው፡፡

 

የዶን ሜካኤል የባሕርይ ድርሻ ደግሞ የሚጫወተው አሁንም አል ፖኪኖ ነው፡፡

 

ከየጡት አባት ክፍል 2 በኋላ ባሉ 15 ዓመታት ውስጥ ሙያው አጠያያቂ ሁኔታ ላይ ለደመረሰበት የፊልም አዘጋጅ ፍራንሲስ ኮፓላ ፓራማውንት የፊልም ካምፓሊ ከገንዘቡ 50 ሚሊዮን ዶላር ሰጥቶታል፡፡ ፍራንሲስኮፓላ በህዝብ ፊት ከዚህ ፊልም ሥራ አጁን ተጣጥቦ ትቶት ነበር፡፡ በ27 ሚሊዮን ዶላር ሊሰራው የሞከረው አንዱ ከልቤ በሚለው ሙዚቃዊ ፊልም ሳቢያ በደረሰበት ኪሳራና እስካሁን ባልተከፈለው የ8 ሚሊዮን ዶላር ዕዳ በካሊፎኒያ ወይም ምርት የተትረፈረፈበት ናፖ ሸለቆ ውስጥ ያለው የቤተሰቡ መኖሪያን አደጋ ላይ ጥሉታል፡፡

 

ይህ 800 ሚሊዮን በዶላር ገቢ ለፖራማውንት ድርጅቱ ያስገኝለትን የማፊያ ታሪክ ለመቀጠል የድርጅቱ ፕሬዘዳንት ፍራንክ ማንኩስ ጥርሰን ሲነክስ በፍራንሲስ ኮፖላም በኩል እሱ በፈለገው መንገድ ለማቅረብ ስምምነት አግኝቷል፡፡

 

ስቱዲዮውም በዚህ ሁኔታ ስለተስማማ ፍራንሲስ ኮፖሳና ማሪዮ ጉዞ /የመጽሐፍ ደራሲ ነው/ ለሳምንታት በሬኖ ሆቴል ውስጥ ተቀመጡ፡፡ ማሪዬ ጉዞ ወደ ዚህ አዲስ ዕቅድ የመጣው በሼክስፕር ድርሰቶች የተሞላ ጭንቅላት ይዞ ነበር፡፡ ለሳምንታት በቲትስ አንድሮ ኒከስ፣ ሮሚዎና ጁሊየት እና በተለይ ንጉስ ሊርን ተመስጦበት ነበር የከረመው፡፡

 

በቀማር ጨዋታዎች መካከል ባሉ እረፍቶች ጸሐፊውና የፊልም አዘጋጁ የፊልም ጽሁፉን አቅናበሩት፡፡ በፊልሙ ቀረጻ ወቅት እስከመጨረሻው ፍጹ ምስጢር ነበር፡፡ ሁሉም ሰው ሶስት ዓይነት አጨራረስ እንዳለውና በሶስቱም መጨረሻ ላይ ሚካኤል ኮርሌዎኔ እንደሚሞት ነበር፡፡

 

ለፍራንሲስ ኮፖላ ይህ ጽንሰ ሃሳብ ለአደጋ የሚገልት ግለት ነው የሚካኤል ኮርሌዎኔን ባህርይ በትክክል በመመርመር በየቱት አባት ላይ ያለው የስልን አያያዙ ከራሱ ሕይወት ማለትም ወይን የማምረት ሥራው የማምረቻ ስቱዲችና፣ የመጽሔት ክፍሉ እ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋ የሄደው የንብረት ግዛቱ ጋር አመሳስሎል፡፡ እስከ ተወሰነ ደረጃ ድረሰ እኔ ሚካኤልን ሆኛለሁ፡፡ ይላል የፊልም አዘጋጁ የጡት አባት ክፍል 3 ውስጥ ያለው ሚካኤል የሼክስፒርን ንጉስ ሊር ይመስለዋል ከላይ በኩል ሞት ሲጠራው ከወደ ሥር ደግሞ ግዛት ሲንሸራተትበትና ሲያመልጠው የሚያሳይ፡፡

 

ይህ የጡት አባት ክፍል 3 የተሰኝው ፊልም ተወዳጅነት የማያተርፍ ከሆነ የ52 ዓመት ዕድሜ ያለው የፈጠራ ሙያ ላይ ማተሚያ ማስጠንቀቂያ ደውሉን ያንቃጭላል፡፡ እናም በስቱዲዮውም በፊልም አዘጋጁም ላይ አደጋው ከፍተኛ ነው፡፡

 

የፊልም ቀረጻሥራው በሮምና በኒውዮርክ እንደቀጠለ በኮርሌዎኔ ታሪክ ላይ ያለው የፍራንሲስ ኮፖላ ጉም የሸፈነው እይታ እየጠራ መጣ፡፡ የፊልም ጽሁፉን እየደጋገመ ነበር የፃፈው፡፡ በፊልሙ ላይ የሚካኤልን ባህርይ ወክሎ የሚጫወተው ተዋናይ አል ፖኪኖም ስለዚህ ሁኔታ ይህ የፊልም ጽሁፍ ሳይሆን ጋዜጣ ነው፡፡ በማለት ቀልዷል፡፡ ተደጋግሞ የተጻፈው ጽሁፍ ግን ፈሩን ይዟል፡፡

 

There are no comments to this entry.

Post New Comment

 BraveJournal Member Non-Member
No Smilies More Smilies »
Please type the letters you see